Afro-Insight News – የካሜሮን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤትን ያልተቀበሉ ተቃዋሚዎች ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ዜጎች ከጸጥታ ሃይሎች በገጠማቸው አጸፋ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። ተቃዋሚዎች የሟቹቹን ቁጥር ወደ አራት ከፍ ያደርጉታል።
ብሬንዳ ቢያ፣ የፕሬዝዳንቱ ሴት ልጅ፣ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ካሜሩናውያን ለአባቷ ድምፅ እንዳይሰጡ የጠየቀችበት ተወዳጅ ቪዲዮ በመለጠፍ ትኩረትን ስባለች።
የካሜሮን ሚዲያዎች ከምርጫው ውጤት መግለጫ አስቀድመው የ92 አመቱ ፕሬዝደንት ፖል ቢያ ዳግም እንዳሸነፉ ፍንጭ የሰጡ ሲሆን ተቃወሚው ኢሳ ቺሮማ ባካሪ እንደተጭበረበረ በመግለጽ ለደጋፊዎቻቸው ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን ገልጿል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በምዕራብ አፍሪካ መፈንቅለ መንግስቶችን መመልከተ የተለመደ ሲሆን የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ፉክክር፥ የምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች እና የህዝቦች በመሪዎቻቸው ያላቸው እምነት ማነስ ቀጠናውን ላመሰው የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደ ምክንያት ይነሳሉ። ከቀናት በፊት በናይጄሪያ ወታደራዊ መሪዎች የተደረገ የመፈንቅለ መንግስትን ሙከራ ምክንያት የፕሬዝደንት ቲኒቡ መንግስት በርካታ ወታደራዊ መሪዎችን አስሯል። በቅርቡ በማሊ፥ ኒጀር፥ ቡርኪናፋሶ እና ጊኒ የተካሄዱ መፈንቅለ መንግስቶች ተካሂደዋል።
አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት – አፍሮ ኢንሳይትን ይከታተሉ።











