Loading...

የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት አመቱ እዲካሄድ ተወሰነ

በየሁለት አመቱ ሲካሄደ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በየአራት አመቱ እንዲካሄድ መወሰኑን የአፍራካ እግርኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ) አስታወቀ።

ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ የተላለፈው የፌደሬሽኑ ስራአስፈጻሚ ኮሚቴ በሞሮኮ ዋና ከተማ ባካሄደው ጉባኔ ሲሆን የካፍ ፕሬዚዳንት ፖትሪስ ሞሴፕ በሰጡት መግለጫ ይፋ ሆኗል።

በግምት 80 በመቶ የሚየሆነውን የካፍ ገቢ የሚሸፍነው እ.ኤ.አ. በ1957 የተጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በየሁለት አመቱ ሲካሄድ ቆይቷል።

በነገው እለት 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በሞሮካ አስተናጋጅነት ይጀመራል። አስተናጋጇ ሞሮኮ ከኮሞሮስ ጋር የመክፈቻ ጨዋታ ታደርጋለች።

ሞስፔ በ2027 በኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ የሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታና በ2028 የሚካሄደው ሌላ ጨዋታ ቀደም ሲል በነበረው መርሃግብር እንደሚቀጥሎ፣ ነገርግን ከእዚያ በኋላ በየአራት አመቱ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ሞስፔ አክለውም ከ2029 ጀምሮ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የአፍሪካ ብሔራዊ ሊግ ጨዋታ በየአመቱ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
“በታሪክ የሀገራት ጨዋታ ዋናኛ የገቢ ምንጫችን ነበር፤ አሁን በየአመቱ የፋይናንስ ምንጭ ይኖረናል” ብለዋል ብለዋል ሞስፔ።

ሞስፔ እንደተናገሩት ይህ ለካፍ የፍይናንስ ነጻነት አስተዋጽኦ የሚያደርግና ከፊፋ መርሃግብር ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።

የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በየአራት አመቱ እንዲካሄድ ቀደም ሲል የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ካፍ ገቢው በዚህ ውድድር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሳይቀበለው ቀርቷል። የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የሚካሄደው የአውሮፖ ክለብ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ወቅት በመሆኑ ክለቦች ተጨዋቾችን እንዲለቁ ስለሚገደዱ አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል።
ይህን የመደራረብ ችግር ለመፍታት ከ2019 ጀምሮ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን ወደ ግማሽ አመት ለመግፋት የተሞከረ ቢሆንም በ2022 በካሜሩንና በ2024 ደግሞ በኮትዲቯር የተካሄደው ጨዋታ በአመቱ መጀመሪያ ሆኗል።
በዚህ አመት በሞሮኮ የሚካሄደው ውድድር ፊፋ የአለም ዋንጫ በሰኔና ሀምሌ እንደሚካሄድ ማሳወቁን ተከትሎ በስድስት ወር ወደ ኋላ ተገፍቷል።

“ይህ በቡድኖች፣ በተጫዋቾችና ክለቦች ፍላጎት የሆነ ነው” ሲሉ ተናግሯል ሞስፔ።
ሞስፔ አክለውም እንደገለጹት የዚህ ውድድር አሽነፊ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኛል፤ ይህም ከኮትዲቫር ዋንጫ ጨዋታ ሽልማት በ3 ሚሊዮን ዶላር ይበልጣል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው