በአሁኑ ወቅት በመላው አፍሪካ “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች” በሚል የሚፈረጁ ተግባራትን የሚከለክሉ ሕጎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጠነከሩ መጥተዋል።
ከሴኔጋል እስከ ጋምቢያ፣ ከጋና እስከ ዩጋንዳ ያሉ ሀገራት ነባር ሕጎቻቸውን በማሻሻልና የእስራት ዘመኑን እስከ ዕድሜ ልክ በማድረስ ጥብቅ አቋም እየያዙ ይገኛሉ። ይህ አዝማሚያ ተራ የሕግ ማሻሻያ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስልቶችን ያቀፈ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ።
በምዕራብ አፍሪካ በኩል የምትገኘው ጋምቢያ በቅርቡ በ2025 ባወጣችው አዲስ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ግብረ-ሰዶማዊነትን በከባድ ወንጀል ፈርጃ እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የሚደርስ ቅጣት ደንግጋለች።
በተመሳሳይ በሴኔጋል ምንም እንኳን ነባሩ ሕግ እስከ 5 ዓመት እስራት የሚደነግግ ቢሆንም በቅርቡ የተካሄዱ የጅምላ እስራቶችን ተከትሎ ቅጣቱ ወደ 10 ዓመት እንዲያድግ የሚጠይቁ አዳዲስ የሕግ ረቂቆች ለፓርላማ ቀርበዋል።
እነዚህ ግለሰቦች “ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ ድርጊቶች” ከሚለው ክስ በተጨማሪ “ኤች አይ ቪን (HIV) ሆን ብሎ ማሰራጨት” በሚል እስከ 10 ዓመት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ተጨማሪ ከባድ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ቅጣቱ ወደ 10 ዓመት እንዲያድግ የሚጠይቁ አዳዲስ የሕግ ረቂቆች ለፓርላማ ቀርበዋል።
እነዚህ እርምጃዎች በአህጉሪቱ ላይ የሚታየውን “የሕግ ማክረር” (Hardening Stance) ግልጽ ማሳያ ናቸው።
ይህ በየሀገራቱ የሚታየው የሕግ ማሻሻያ ግፊት (Strategic Rise) ከሁለት አቅጣጫ የሚመነጭ ስልታዊ እርምጃ እንደሆነ ይነገራል።












