በቻይና የልማት ትኩረቶች ይፋ የሚሆኑባቸው በተመሳሳይ ወቅት የሚካሄዱ ሁለት ወሳኝ ስብሰባዎች(Two Sessions) በየአመቱ ይካሄዳሉ። አንደኛው ብሔራዊ የህዝብ ኮንግረስ(NPC) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የቻይና ህዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ኮንፈረንስ(CPPCC) ነው።
በእነዚህ ስብሰባዎች ወቅት የሀገሪቱ ህግ አውጭዎችና የፖለቲካ አማካሪዎች በቤጂንግ በመሰባሰብ ያለፈውን የመንግስት ስራ አፈጻጸም በመገምገም የወደፊቶቹን የልማት ትኩረቶች ያስቀምጣሉ። የዘንድሮዎቹ ስብሰባዎች ከ15ኛው የአምስት አመት የልማት እቅድ(2026-2030) መጀመር ጋር የተገጣጠሙ መሆናቸው የተለዩ አድርጓቸዋል።
ቻይና ይፋ ያደረገቸው የ2026ቱ የልማት እቅድ ዋና አላማው በፈጠራ የታገዘ ልማት እውን ማድረግ ነው። በርግጥ ቻይና ለቴክኖሎጂ ትኩረት መስጠቷን ያሳየችው አዲስ አመቷን ባከበረችበት ባለፈው ወር ነበር። ቻይና አለምን ያስገረመ በሮቦቶች የታጀበ ትዕይት በማቅረብ ነበር በቴክኖሎጂ መሪ ለመሆን ያላትን ፍላጎት የገለጸችው።

በብሔራዊ የህዝብ ኮንግረስ(NPC) ስብሰባ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር(Premiere) ሊ ኪያንግ በአምስቱ አመት እቅድ ውስጥ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠይቁ ኢንዱስትሪዎች፣ የኢኮኖሚ ማስተካከያዎች እንዲሁም ፈጠራና የጥናት ኢንቨስትመንት ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት በ2026 ቻይና ከ4-5 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ አቅዳለች። ሀገሪቱ ለፈጠራ ትኩረት የሰጠችው ከሌላው አለም ጋር የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችላት ዘርፍ በመሆኑ ነው።
ሲጂቲኤን እንደዘገበው ቻይና ዘላቂ የሆነና በፈጠራ የታገዘ የእድገት አማራጭ እንደምትከተል ግልጽ አድርጋለች።
የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳይ በአመቱ ዋና ትኩረት ተሰጥቶታል። አለምአቀፍ የኢኮኖሚ ስርአቱ ባለመረጋጋቱ ምክንያት ቻይና ትኩረቷን በሀገር ውስጥ ፍላጎት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና በኢንዱስትሪ መሻሻል ላይ አድርጋለች።
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በአረንጓዴ ልማትና በዘመናዊ ማንፉቸሪንግ(ኢንዱስትሪ) ዙሪያ ወይይቶች መካሄዳቸው ቻይና በቁልፍ ቴክኒዎሎጂዎች እየተወዳደረች ኢኮኖሚዋን ለማጠናከር እንዳለመች የሚያሳዩ ናቸው።
አብዛኛውን ጊዜ ቻይና የምታስቀምጣቸው የልማት እቅዶች ረጅም ጊዜ የሚሸፍኑ መሆናቸው የአለምን ትኩረት እንዲስቡ ያደርጋቸዋል። የፖለሲ መዋቅር መሪዎች በአምስት አመት ውስጥ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የልማት ስራዎችን ለማቀናጀት ይችላሉ።
በፈጠራም ይሁን በኢኮኖሚ ሪፎርም ወይም በረጅም ጊዜ እቅድ፣ በቤጂንግ የሚወጡ ፖሊሲዎች በመጭዎቹ አመታት የቻይናን አካሄድና በአለም የሚኖራትን ሚና የሚወስኑ መሆናቸው ይታወቃል። አፍሪካን ጨምሮ ቀሪው አለምም ከቻይና ለመጣጣም የሚያሰችል ፖሊሲ ለመቀየስ እድል የሚያገኘው በስብሰባዎቹ ከሚወጡ አጀንዳዎች ነው።
የዜና ምንጭ: CGTN











