Loading...

አወዛጋቢ ቦታዎች በፌደራል መንግስት ስር ሆነው የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ብቻ እንዲያካሂዱ ተወሰነ

የአማራ እና የትግራይ ክልል መንግስታት የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው እና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት “አወዛጋቢ” የተባሉት ቦታዎች ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ብቻ እንደሚካሄዱ የፌደሬሽን ምክር ቤት ለምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን ቦርዱ በዛሬው እለት የካቲት 16፣2018 ዓ.ም አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ይህን ደብዳቤ የጻፈው ምርጫ ቦርድ ባለፈው ወር አወዛጋቢ በተባሉት ቦታዎች ያሉትን አምስት የምርጫ ክልሎች በትግራይ ክልል ስር ካሉ የምርጫ ክልሎች ስርዝር ውስጥ አካቶ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። ፌደሬሽኑ ውዝግቡ እስከሚፈታ ድረስ የሁመራ፣ የአዲረመጽ፣ የኮረም እፍላ፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ የምርጫ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ምርጫ ብቻ ይካሄዳል።

በዚህ ውሳኔ መሰረት አካባቢዎቹ በየትኛውም ክልል ውስጥ ታቅፈው ምርጫ ስለማያካሄዱ የክልል ምክር ቤት ተወካዮች ምርጫ አይካሄድም።

ቦርዱ የፌደሬሽን ምክር ቤት ባስቀመጠው ትዕዛዝ መሰረት 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደሚያከናውን ገልጿል።

የይገባኛል ጥያቄ የተነሳባቸው አካባቢዎች ጥቅምት 24፣2013ዓ.ም በፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በትግራይ ክልል ስር ነበሩ። ይሁን እንጅ እነዚህ አካባቢዎች በኃይል ወደ ትግራይ ክልል እንደተካተቱና የማንነት ጥያቄ እንዳላቸው ጥያቄዎች ለረጅም ጊዜ ሲቀርቡ ቆይተዋል።

ጦርነቱን የቋጨው የፕሪቶሪያ ስምምነት እነዚህን ቦታዎች “አወዛጋቢ” (Contested area) የሚል አንቀጽ በማስገባት የየትኛውም ከልል ግዛት እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።

በቀድሞው የህወሓት ባለስልጣን እና በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ስምረት ፖርቲ የፌደሬሽኑን ውሳኔ በጽኑ አውግዟል።

ይህ ውሳኔ የሀገሪቱን ህገ መንግስታዊ ስርአት የሚንድ…” እንደሆነ የገለጸው ፓርቲው ሞክር ቤቱ የምሮጫ ክልሎችን የማዋቀር ስልጣንና አካባቢዎች ከነባር አስተዳደራቸው ውጭ አስወጥቶ በፌደራል መንግስት ስር የማድረግ ስልጣን የለውም ብሏል።

የፌደራል መንግስት ውዝግቡ በህዝብ  ውሳኔ ይፈታል የሚል አቋም ይዟል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው