Loading...

የሶማሊያ እና ግብጽ መሪዎች በካይሮ ተገናኙ፤ ቀይ ባህር የንግግራቸው አካል ነበር

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼህ መሃሙድ ወደ ካይሮ ግብጽ ተጉዘው ከግብጹ አቻቸው አል ሲሲ ጋር በጋራ የልማት ትብብር፣ ወታደራዊ ስምምነታቸው እና የቀይ ባህር ደህንነትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።

በተለይም ግንኙነቱ አል ሲሲ የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ ደህንነትን የማስጠበቅ ስልጣን ባህሩን የሚያዋስኑ አገራት ብቻ መሆኑን ዳግም የገለጹበት ነበር። ግብጽ እና ሶማሊያ የባህሩ የሰሜን እና የደቡብ መግቢያ ነጥቦች ላይ የሚገኙ መሆናቸው ለአገራቱ ሃላፊነትን የሚጥልባቸው ጂኦግራፊያዊ እውነታ እንደሆነ አልሲሲ ተናግረዋል።

ሶማሊያ ለእስራኤል ያስተላለፈችው ጠንካራ ማስጠንቀቂያ

ፕሬዝደንት አሰን ሼህ ወደ ግብጽ ከመጓዛቸው አስቀድሞ የእስራኤል እና የሶማሊላንድ ግንኙነት ላይ ባተኮሩ ጉዳዮች ላይ ከአልጄዚራ ጋር ቃለ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እስራኤል የጦር ቤዝ በሶማሊላንድ የማቋቋም አላማ እንዳላት ተናግረዋል። ፕሬዝደንቱ “እስራሴል በመጨረሻ ጦሯን ወደ ሶማሊላንድ ለማስፈር ወደ እንቅስቃሴ የገባች ቀን ሶማሊያ እራሷን ለመመከት ትገደዳለች” ብለዋል።

እስራኤል በቀጠናው የጦር ቤዝ ማቋቋሟም ሶማሊላንድን ለመወዳጀት ምክንያት ከሆኗት ሶስት ጉዳዮች መሃል እንደሆኑ የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ የተቀሩት ሁለት ምክንያቶች ሶማሊላንድን የአብርሃም አኮርድ አባል ማድረግ እና ፍልስጤማውያንን በሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛት ላይ ማስፈር ናቸው ብለዋል።

ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ስለ ግብጽ የተሰማቸው ስጋት

የአል ሲሲ እና የሐሰን ሼህ መሃሙድ ግንኙነት እስራኤል ከሶማሊያ በተጨማሪ ከግብጽ ጋር የገባቸበትን ውጥረት ተከትሎ የተከናወነ ነበር።

ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በእስራኤል ፓርላማ የዝግ ስብሰባ ላይ “የግብጽ ጦር በእጅጉ እየተጠናከረ ነው፥ ልንቆጣጠረው ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

ግብጽ እና እስራኤልን በሚያዋስነው ሰንዓ በረሃ ላይ የግብጽ ጦር ከፍተኛ ወታዳራዊ እንቅስቃሴ እያደረገች እንደሆነ በመጠቆም አሜሪካ ግብጽ ላይ ጫና እንድታደርግ ኔታኒያሁ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ግብጽ በተቃራኒው በበረሃው ላይ የምታደርገው ወታዳራዊ አንቅስቃሴ ፍልስጤማውያን “ከገዛ መሬታቸው በግዴታ ከጋዛ እንዳይፈናቀሉ” ለመቆጣጠር የምታደርገው እንደሆነ ስትገለጽ ቆይታለች።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው