Loading...

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የመጀመሪያውን የAI ዩኒቨርሲቲን ልትመሰርት ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም ማቀዳቸውን አስታውቀው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ የዝግጅት ስራ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ 1,000 ያህል ተማሪዎችን አስተምሮ ያስመርቃል ከነዚህም 100ዎቹ በስኮላርሺፕ እድል የሚመረጡ እንደሆነ ገልጸዋል። ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ሁለት የስኮላርሺፕ ቦታዎችን ለመመደብ መታቀዱንም ተናግረዋል።

ከጠቅላላ አመልካቾች በመጨረሻ የትምህርት እድሉን የሚያገኙት እስከ ሁለት በመቶ የሚደርሱት እንደሆነ በመናገር፥ እድሉን ለማግኘት ከፍተኛ ፉክክር የሚደረግበት እና የልህቀት ተቋም እንደሚሆን አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ተቋሙን በአሀኑ ሰዓት በአለም ዙሪያ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ከተመሰረቱ የAI የትምህርት ክፍሎች ለየት የሚያደርገው ሙሉ ለሙሉ AI ላይ ያተኮረ በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል።

የተቋሙ አላማ Natural language processing,ሮቦቲክስን, የmachine learning፣ እና የመሳሰሉትን የAI ጥናቶችን በመሰጥት፥ ጥቂት ነገር ግን ከፍተኛ ችሎታ ያለው በተግባር የሰለጠነ የሰው ሃይል መፍጠር ነው ብለዋል።

ይህን እቅድ ይፋ ያደረጉት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተቋሙ ምሁራን እና የትምህርት ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት መድረክ የፓናል ጥናት አቅርበዋል። በንግግራቸውም የAI ዩኒቨርሲቲው ከመንግስት ሰፊ የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነት የማጠናከር ራዕይ ጋር አያይዘውታል።

ዩኒቨርሲቲው በ2023 ዓ.ም. አገሪቱን የአፍሪካ የእድገት አርአያ እንድትሆን እና በ2040 ዓ.ም. በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን ለማድረግ ያለመውን የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት ስትራቴጂ አካል መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የሰብአዊ ክብር ማረጋገጥ፥ የውጭ ዕርዳታ ጥገኝነት ማስቀረት እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የብድር ደረጃ ማሻሻልን ከተለመው ሰፊ እቅድ ጋር አያይዘውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተቋሙ ለኤአይአይ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በፍጥነት ተግባራዊ ከሆነ በአለም ላይ በዓይነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው