Loading...

ታዋቂ አርቲስቶችንና የፊንቴክ ባለቤቶች በከፍተኛ ማጭበርበር ተጠርጥረው ተከሰሱ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት ባለቤቶች የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስና ግርማይ ገብረሚካኤል “ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በመጠቀም ከ1,200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት” በማድረስ ተጠርጥረው ክስ እንደተመሰረተባቸው አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገጸው በ19 የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ካደረገ በኋላ ውጤቱን ለአቃቤ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትባቸው ማድረጉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ዳንኤል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩን ማረሚያ ቤት ውስጥ ሆኖ እየተከታተለ ነው ያለው ፖሊስ ሌላኛው ተጠርጣሪ ግርማይ አለመያዙንና እየተፈለገ መሆኑን ገልጿል። ፖሊስ እንዳለው እነዚህ ግለሰቦች ከቻይናው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ (BYD)  ጋር ውል ሳይኖራቸው፣ ውል ያላቸው በማስመሰልና ደንበኞች 50 በመቶ ቅድመ ክፍያ ከከፈሉ በ90 ቀናት ውስጥ የመኪና ባለቤት እንደሚሆኑ በመግለጽ ማጭበርበር ፈጽመዋል።

ተጠርጣሪዎች ከእያንዳንዱ ተጎጂ ለቅድመ ክፍያ፣ ለመንግስት ታክስና ለቻርጀር ማሰሪያ በሚል 1.365 ሚሊዮን ብር ስብስበዋል ብሏል ፖሊስ

ፖሊስ ከፊንቴክ ባለቤቶች በተጨማሪ ድርጅቱን “ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ” በህገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጠቅመዋል ያላቸውን አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ከሷል። ከድርጅቱ ጥቅም ተጋርተዋል በሚል ከተከሰሱት አርቲስቶች ውስጥ ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝና  ይገረም ደጀኔ ይገኙበታል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው