ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማዘዋወር ወንጀል ተጠርጥሮ በአለምአቀፍ ደረጃ ሲፈለግ የነበረው ይትባረክ ዳዊት ወይም ክብሮም ከእነተባባሪዎቹ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል ።
መንግስታዊው ኢቢሲ ፖሊሲን ጠቅሶ እንደዘገበው ይትባረክ ከሌሎች 9 ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን 3000 በላይ ሰዎች በህገወጥ መንገድ እንዲዘዋወሩ፣ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያልፍና ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ አድርጓል።
ግለሰቡ በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማው ውስጥ መያዙንና የወንጀል ምርመራውን አጠናቆ ጉዳዩን ለአቃቤ ህግ መላኩንም ፖሊስ ገልጿል። በፓስፖርት ስሙ ይትባረክ ተብሎ የሚጠራው ይህ ተጠርጣሪው በርካታ የሀሰተኛ ሰሞችን እንደሚጠቀም ፖሊስ ጠቅሷል።

ተጠርጣሪዎቹ በወንጀል ያፈሩት ሀብትና በባንክ የሚገኝ ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እንዲታገድ ማድረጉን የገለጸው ፖሊስ ህገወጥ አዘዋዋሪ ቡድኑ ከ2010 ጀምሮ ወጣቶችን ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከጁቡቲ፣ ከሶማሊያና ከኬንያ ወደ ሊቢያ ወስዶ በማገት ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲልኩ ሲያስገድድና ያልተላከላቸውን ደግሞ በማሰቃየት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲፈጽም ቀይቷል ፖሊስ።
ፓሊስ የተጠርጣሪዎቹን በወንጀሉ መሳተፍ ለማስረዳት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከ16 ተጎጂዎች ማስረጃ መቀበሉንም ገልጿል።
ፓሊስ ዋና ተጠርጣሪውን ይትባረክ ለመያዝ የቻለው በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሚሠራው “The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ከተባለ ድርጅት ጋር የመረጃ ልውውጥ በማድረግ መሆኑን ጠቅሷል።












