Loading...

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  እስራኤልን ጎበኙ

የህንዱ  ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ገብተዋል።

ሞዲ በእስራኤል ፓርላማ (ኬንሴት) ንግግር እንደሚያደርጉና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁና ፕሬዝደንት አይዛክ ዜርዞግ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ሞዲ ከፍልስጤማውያን አመራሮች ጋር ንግግር ለማድረግ መርሃግብር አልያዙም።

ይህ ጉብኝት የመጣው ሁለቱ  ሀገራት በመከላከያ፣ በቴክኖሎጂና በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ሞዲ ወደ ስልጣን ከመጡ ከአስርት አመት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል።

ጉብኝቱ የመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቿን ላለማስከፋት የምትሞክረውን ህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚፈትን ቢቢሲ ዘግቧል። ሞዲ እኤአ በ2017 እስራኤልን በመጎብኘት የመጀመሪያው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው