Loading...

የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ተከትሎ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመከፈት ተስማማች

ኢራን እስራኤልና አሜሪካ ተቀናጅተው የከፈቱባትን ጦርነት ተከትሎ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ዘግታው የነበረውን የሆርሙዝ ስርጥ ለሁለት ሳምንታት ለመክፈት ተስማምታለች።

ኢራን መስማማቷን ያስታወቀችው፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ በፓኪስታን የቀረበውን የስምምነት ነጥብ ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትናንት እለት ኢራን ሰርጡን የማትከፍት ከሆነ የኢራንን ስልጣኔ “ሙሉ በሙሉ እንዳልነበረ” የሚያደርግ እርምጃ እንደሚወስዱ የሰጡት ማስጠንቀቂያ ሰአታት ሲቀረው፣ የፓኪስታን አሜሪካ ጥቃቷን እንድታቆምና በምላሹ ኢራን ሰርጡን ለሁለት ሳምንት እንድትከፍት ያቀረቡት ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል።

ኢራን ሰርጡን “ሙሉ በሙሉ፣ በፍጥነትና ደህነነቱ በተጠበቀ ሁኔታ” ለመክፈት መስማማቷን የገለጹት ትራምፕ አሜሪካ ልታደርሰው የነበረውን ከባድ ጥቃት ለሁለት ሳምንታት እንደሚያቆሙ ገልጸዋል።
“ከኢራን ባለ 10 ነጥብ ሀሳብ ተቀብለናል፤ ይህ ለስምምነት መሰረት ይሆናል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

አሜሪካና ኢራን በአብዛኞቹ አከራካሪ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውንና ተኩስ አቁሙ ተግባራዊ በሚሆንባቸው ሁለቱ ሳምንታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚቻል ገልጸዋል።

የአለም 1/5 የሚሆነው ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት አለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት አስከትሏል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው