Loading...

ኬንያ 2000 በላይ ጉንዳኖችን ከሀገር ይዞ ሊወጣ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች

ከ2000 በላይ ህይወት ያላቸው የጋርደን ጉዳኖችን በሻንጣው ይዞ ሊወጣ የነበረ ግለሰብ በናይሮቢ አየር ማሪያ በዚህ ሳምንት በቁጥጥር መዋሉ ተገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኬንያ እነዚህን ጉንዳኖች በህገወጥ መንገድ ይዞ ለመውጣት እየሚደረጉ ሙከራዎች እየጨመሩ ናቸው።

ሮይተርስ እንደዘገበው ባለፈው ማክሰኞ ዛንግ ኪዩን የተባለው የ27 አመት ቻይናዊ ግለሰብ  ጉንዳኖቹን ይዞ ሊወጣ ሲል በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዟል። ዛንግ ባለፈው አመት ከመያዝ ካመለጠ በኋላ የኢምግሬሽን ባለስልጣናት በፓስፖርቱ ላይ እግድ ጥለው ነበር።

የጉንዳን አፍቃሪ ሰዎች(ant afuctionados) ጉንዳኖችን ፎርሚካራምስ በተባሉ ብርሃን አስተላላፊ ቱቦዎች ውስጥ በማስቀመጥ ስነ ህይወታቸውን ለመመልከት ብዙ ገንዘብ ይከፍላሉ። ባለፈው አመትም ለኬንያ ስነ ምህዳር አስፈላጊ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ  ጉንዳኖችን ለማውጣት የሞከሩ አራት ሰዎች እያንዳንዳቸው 7700 ዶላር ገንዘብ  መቀጣታቸው ይታወሳል።

ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ይህ ክስተት የእንስሳት አካል አዘዋዋሪዎች(biopirats) ከተለመዱት እንደ ዝሆን ጥርስ ከመሳሰሉት ብዙም ወደማይታወቁት ዝርያዎች መሸጋገራቸውን የሚያሳይ ነው።

የዛንግ ሻንጣ ሲመረመር በቴስት ቱቦዎች (በቀጭን ቱቦዎች) ውስጥ የታሸጉና በሶስት የሶፍት ወረቀቶች የተጠቀለሉትን 1948 ጨምሮ በአጠቃላይ 2238 ጉንዳኖች መገኘታቸውን መርማሪዎች ገልጸዋል። መርማሪዎች ዛንግ በኬንያ ለሁለት ሳምንት መቆየቱንና ጉንዳኖቹን ያቀረቡለትን ሶስት ተባባሪዎች መጥቀሱን ተናግረዋል።

የኬንያ የዱር እንስሳት አገልግሎት ከዛንግ የተወሰዱ አይፎን እና ማክቡክ ኮምፒዩተሮችን ጨምሮ ምርመራውን ለመጨረስ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

በተመሳሳይ ከኬንያ የወጣ ጉንዳን በባንኮክ ማክሰኞ መያዙን የገለጸው የዱር እንስሳት አገልግሎቱ፣ ይህ ሰፊ የሆነና የተቀናጀ ጉንዳኖችን በህገወጥ መንገድ የማስወጣት መረብ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብሏል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው