የሰው ልጆች ከዛሬ አምሳ አመታት በፊት ወደ ጨረቃ ካደረጉት ጉዞ በሗላ፥ የናሳ የአስትሮናቶች ቡድን ወደ ጨረቃ በማምራት ታሪክ ለመስራት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ተልዕኮው አራት አስትሮኖቶችን የሚይዝ ሲሆን ጠቅላላው የጉዞ ቆይታ 10 ቀናት ይፈጃል። ጉዞው በዚሁ አመት፥ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
Artemis II (አርቴሚስ ሁለተኛ) የተባለው የህዋ ተልእኮ፥ የሰው ልጅ በታሪኩ ከምድር ጠለል ርቆ የተጓዘው ረዥሙ ጉዞ ይሆናል። ከዚህ ቀደም ሪከርዱ ተይዞ የነበረው እ.ኤ.አ. በ1970 የተረደገው አፖሎ 13 የተባለው 400171.432 ኪሎ ሜትሮችን የፈጀው ጉዞ ነበር።
ሆኖም የጉዞው ግብ ጨረቃ ላይ ማረፍ ሳይሆን በቀጣይ በጨረቃ ላይ ለማረፍ ለሚደረገው ጉዞ እንደሙከራ የሚደረግ ነው።
አስትሮናቶቹ በጨረቃ ላይ ሳያርፉ በቅርብ ርቀት ጨረቃን እየዞሩ መረጃችን በማሰባሰብ በ2019 በጨረቃ ላይ ለማረፍ ለሚደረገው Artemis III(አርቴሚስ ሶስተኛ) ጉዞ አመቺ ሁኔታዎችን ያጠናሉ።












