የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ በሚልኩ ወኪሎች እና ኔትወርኮች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ባንኩ በሕገ-ወጥ ወኪሎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በእነዚህ አካላት በኩል ገንዘብ በሚቀበሉ ግለሰቦች ላይም አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሩን ገልጿል።
ባንኩ ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ባስተላለፈው ጥሪ፣ በሀገር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው የባንክ ሂሳብ እንዳይዘጋ ወይም እንዳይቋረጥ ሲሉ፣ ፈቃድ በሌላቸው ወኪሎች በኩል ገንዘብ ከመላክ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሌላቸው ሲል የለያቸው ወኪሎች፦
- Shegey Money Transfer
- Adulis Money Transfer (ADZ0)
- Red Sea
- Avanti
- World Direct Link
- Rasmy Pay
- USwyre
- Zola
- Taaj Financial Services
ባንኩ የእነዚህን ወኪሎች አገልግሎት መጠቀም ላኪዎችንም ሆነ ተቀባዮችን ለከባድ ሕጋዊ ተጠያቂነት ሊያጋልጥ እንደሚችል አፅንዖት ሰጥቶ አስገንዝቧል።












