Loading...

የቴክኒክ ብልሽት ያጋጠመውን የመንገደኞች አውሮፕላን ባህር ዳርቻ ያሳረፈው አብራሪ ተወደሰ

በሶማሊያ የሚገኘው አየርመንገድ የቴክኒክ ብልሽት ያጋጠመውንና 55 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረውን አውሮፕላኑን በሞጋዲሹ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኝ የባህር ዳርቻ ያሳረፈውን አብራሪ አወደሰ።

ፎከር 50 የተባለው አውሮፕላን ማክሰኞ ጠዋት ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ችግር እንዳጋጠመው የበረራ ሰራተኞች ሪፖርት ማድረጋቸውንና ለመመለስ መጠየቃቸውን የሶማሊያ ሲቪል አቬሽን(ሲሲኤ) ባለስልጣን አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ መቆም አለመቻሉንና የመንደርደሪያ ቦታውን ጥሶ በባህር ዳርቻ መቆሙን የሲሲኤ ዳይሬተር አህመድ ማካሊን ሀሰን ተናግረዋል።

የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም ተብሏል።
በኤክስ ገጽ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ ወርደው ከባህሩ ወደ ዳር ሲወጡ ያሳያሉ። በአደጋው ከባድ ጉዳት አልተመዘገበም።

በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ልኡክ እንደገለጸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ህይወት ለማዳን በፍጥነት ወደ ስፍራው ተሰማርተው ነበር። የሶማሊያ የትራንስፖርት ሚኒስትርም በቦታው እንደነበሩ ልኡኩ አክሎ ገልጿል።

“ሁሉም ተሳፋሪዎችና የበረራ ሰራተኞች ጉዳት አልደረሰባቸውም። አውሮፕላኑ በድንገት ለማረፍ እንዲጠይቅ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራዎች እየተደረጉ ነው” ሲሉ የስታርስካይ ቃል አቀባይ ሀሰን ሞሀመድ አደን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ “የአብራሪው ፈጣን ወሳኔ ተሳፋሪዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው በማድረግ ወሳኝ ሚና ነበረው፤ ሁኔታውን የያዘበት መንገድ የሚመሰገን ነው” ብለዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው