ኒሪ የተባለ የሩሲያ ኒውሮቴክ ኩባንያ እርግቦችን ወደ “ባዮድሮኖች” ወይም በርቀት ቁጥጥር የሚደረግባቸው መቆጣጠሪያ እየቀየረ ነው።
በሞስኮ ውስጥ የወፎች አንጎል ላይ ኒውሮቺፖችን በመግጠም እና ጀርባቸው ላይ የጂፒኤስ መቆጣጠሪያ በማድረግ የተሳካ የባዮድሮን ሙከራ አድርገዋል።
ይህ ዘዴ የሚሰራው ኤሌክትሮዶችን የወፍ አንጎል ላይ በመትከል ሲሆን፥ ይህም ኦፕሬተሮች ወፎችን ማሰልጠን ሳይጠበቅባቸው የኤሌክትሪክ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ብቻ ወፎቹን ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ መምራት ያስችላቸዋል።
ኩባንያው እነዚህ በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ መሳሪያዎች የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ራቅ ያሉ ቦታዎችን ከመደበኛ ድሮኖች በበለጠ በመጓዝ ብዙ አከባቢዎችን በብቃት መቃኘት እንደሚችሉ ተናግሯል።
የኩባንያው ዌብሳይት ላይ የሰፈረው መረጃ እንደሚያስረዳው፥ የዚህ ፈጠራ ዋና አላማው የአካባቢ እና የኢንዱስትሪ ቅኝት፣ የፍለጋ እና የማዳን ስራዎችን እና ተጨማሪ የሴፍቲኔትን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት ክትትል ማድረግ ነው።
ኩባንያው እነዚህ በጸሃይል የሚሰሩ መሳሪያዎች የተገጠሙላቸው ወፎች የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ራቅ ያሉ ቦታዎችን ከመደበኛ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በበለጠ በብቃት መከታተል እንደሚችሉ ተናግሯል።
ኒሪ ይህንን ቴክኖሎጂ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት ወደ ቁራዎች እና የባህር ወፎች ላይ ለማስፋፋት እንዳቀደም ተገልጿል።
ኒሪ የተባለው ይህ ድርጅ ታደያ ይህንን ቁራዎች እና ሲገሎች(የባህር ወፎች) ላይ በመተግበር ሊኢንዱስትሪ አገልግሎት ማዋል ያስባል።











