Loading...

ደቡብ አፍሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የአደራዳሪነት ሚና ለመወጣት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

ደቡብ አፍሪካ እድሉ የሚሰጣት ከሆነ እስራኤልና አሜሪካ በቅንጅት ከኢራን ጋር እያደረጉት ባለው ግጭት ውስጥ የአደራዳሪነት ሚና ለመወጣት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ተናግረዋል

ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በቅንጅት በመሆን ኢራን ውስጥ ከባድ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ነው። በዘመቻው የመጀመሪያ ቀን የኢራን ጠቅላይ መሪና ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች ተገድለዋል። በዚህ ምክንያት ኢራን ሚሳይል በማስወንጨፍ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች ሲሆን እስራኤልንና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ አድርጋለች።

ራማፎሳ “ደቡብ አፍሪካ የአደራዳሪነት ወይም ሌላ ሚና ለመጫወት ፈቃደኛ ነች። እድሎች ክፍት ከሆኑ ወይም ከተጠየቅን፣ ኃላፊነታችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን” ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም እድሉ ከተገኘ ተኩስ እንዲቆምና ግጭቱ በድርድር እንዲፈታ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ግጭቱ ሲቀጥል፣ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ሲሆን ኢራንም ወደ እስራኤልና ወደአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ሚሳይል ማስወንጨፏን አላቆመችም።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው