Loading...

በ2026ቱ የፊፋ አለም ዋንጫ ጨዋታ የአፍሪካ ቡድኖች ምድብ ድልድል ምን ይመስላል?

የ2026ቱ የፊፋ አለም ዋንጫ የምድብ ድልድል በትናንትናው እለት በአሜሪካ ዋሽንግተን በተካሄደ ስነስርአት ይፋ ሆኗል።

የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ ሲካሄድ የአስተናጋጅ ሀገራት መሪዎች የሆኑት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይና የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼንባውም ተገኝተዋል።

ፊፋ በአለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ የሚሳተፉ ሀገራትን ቁጥር ከፍ ማድረጉን ተከትሎ የተሳታፊ የአፍሪካ ቡድኖችም ቁጥር 9 ደርሷል። በዚህ ውድድር አፍሪካ በአልጄሪያ፣ ኬፕ ቨር፣ ግብጽ፣ ጋና፣ ኮት ዲቮር፣ ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካና ቱኒዚያ ትወከላለች።

እነዚህ ሀገራት የተካተቱባቸው ምድቦች የሚከተሉት ናቸው፦

ደቡብ አፍሪካ በምድብ ኤ፥

  • ደቡብ አፍሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ አንድ የዴንማርክ ጨዋታ፣ ሜቄዶንያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ ወይም አየርላንድ

ሞሮኮ በምድብ ሲ፥

  • ብራዚል፣ ሞሮኮ፣ ስኮትላንድና ሀይቲ

ኮትዲቮር በምድብ ኢ፦

  • ኮት ዲቮር፣ ጀርመን፣ ኢኳዶርና ኩራኳኣ

ቱኒዚያ በምድብ ኤፍ፦

  • ቱኒዚያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ጃፓን፣ ስዊድን፣ ፖላንድ፣ አልባንያና የዩክሬን አንድ ጨዋታ

ግብጽ በምድብ ጂ፦

  • ቤልጅየም፣ ኢራን፣ ግብጽና ኒውዝላንድ

ኬፕ ቨርዴ በምድብ ኤች፦

  • ኬፕ ቨርዴ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ስፔንና ኡራጓይ

ሴኔጋል በምድብ አይ፦

  • ሴኔጋል፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ቦልቪያ ወይም ሱርኔምና የኢራቅ አንድ ጨዋታ

አልጄሪያ በምድብ ጄ፦

  • አርጀንቲና፣ ኦስትሪያ፣ ጆርዳንና አልጄሪያ

ጋና በምድብ ኤል፦

  • ጋና፣ ኢንግላንድ፣ ክሮሺያና ፓናማ

የ2026ቱ የአለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ሜክሲኮና በካናዳ በጋራ አስተናጋጅነት እ.ኤ.አ. ከሰኔ 11 እስከ 19፣2026 ድረስ ይካሄዳል።

ወድድሩ በሜክሲኮ፣ ሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም ተጀምሮ በአሜሪካ ኒው ጄርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስቴዲየም ይጠናቀቃል።

በኳታር አስተናጋጅነት የተካሄደውን የ2022ቱን የአለም ዋንጫ ደቡብ አሜሪካዊቷ አርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምት ማሸነፏ ይታወሳል።

የ2016ቱ የአለም ዋንጫ ወድድር ፎርማት

ውድድሩ ከፍጻሜው በፊት አንድ በዙር የሚደረግ የቡድን ጨዋታና አራት የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ይኖሩታል። ከዚህ በፊት ከነበሩት የፊፋ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች በተለየ መልኩ የጥሎ ማለፍ ውድድሩ በ32 ሀገራት የሚጀምር ሲሆን 16 ቡድኖች ያሉበት ዙር፣ አራት ሩብ ፍጻሜዎችና ሁለት ግማሽ ፍጻሜዎች በተከታታይ ይካሄዳሉ።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው