Loading...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፉል ጋር የኢትዮጵያና ጀርመን ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ መምከራቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እንዳስታወቀው ጆአን ዋድፉል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ አቀባበል እንደተደረገላቸውና ጀርመንና ኢትዮጵያ ከ120 አመታት በላይ የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እያከበሩ ባለበት ወቅት ነው።

ሚኒስቴሩ አምባሳደር ሀደራ ጀርመን በ2025-27 ትብብር ማዕቀፍና የለውጥ ስራዎችን፣ አረንጓዴ ልማትን፣ ቀጣናዊ ሰላምና የህዝብ ለህዝብ ስራዎችን በመደገፍና ያላትን አስተማማኝ አጋርነት ጠቅሰዋል።

ይህ ጉብኝት በተለይ በታዳሽ ኃይል፣ በመሰረተልማት፣ በግብራና በግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያና በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፉ ትኩረት እንደሚያደርግ አምባሳደሩ መናገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው