Loading...

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያዊ ለዩጋናዳ አየር መንግድ መሪነት ታጩ

ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ የቀድሙውን የኢትዮጵያ አየር መንግድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄን እንዳጩ The Nile Post ዘግቧል።

አቶ ግርማ ዋቄ የቀድሞዋን የዩጋንዳ አየር መንግድ ስራ አስፈጻሚዋን ጄኒፈር ባሙቱራኪ የሚተኩ ሲሆን ስራ አስፈጻሚዋ በፕሬዝደንት ሙሴቪኒ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።

የሙሴቪኒ መንግስት ባለፉት ወራት የዩጋንዳ አየር መንግድ ላይ ከብልሹ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ምርመራን ከፍቶ የነበረ ሲሆን የዩጋንዳ አየር መንግድ ጠቅላላ አስተዳደሩን በመለወጥ አለም አቀፍ ቁመናውን ለማዘመን እንዳሰበ ዘገባው ያስረዳል።

አቶ ግርማ ዋቄ በሙያቸው ከፍተኛ ስኬት እና ምስጉንነትን ያገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንግድን ከ1996 እስከ 2003 ዓ.ም በዋና ስራ አስፈጻሚነት እና ከ2014 እስከ 2015 ዓ.ም ደግሞ በቦርድ ሊቀመንበርነት አገልግለዋል። አቶ ግርማ ከኢትዮጵያ አየር መንግድ በሗላም በሩዋንዳ አየር መንገድ የቦርድ ሊቀመንበር እና ለቶጎ መንግስት የበረራ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ሰርተዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የድርሻ ባለቤት የሆነበት የምዕራብ አፍሪካው ASKY አየር መንግድ ምስረታ አስተዋጽዖ ያደረጉ ነበሩ።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው