Loading...

ኢራን ጠቅላይ መሪው ኻሚኒ መገደላቸውን አረጋገጠች

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው የእስራኤል እና የአሜሪካ የተቀናጀ የአየር ጥቃት መገደላቸውን የኢራን መንግስት መገናኘ ብዙኻን ዘግበዋል።

በጥቃቱ ከኻሚኒ በተጨማሪ ልጃቸው፣ አማቻቸው እና የልጅ ልጃቸው አብረው ተገድለዋል።

ቅዳሜ ጠዋት እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመሆን ለህልውናዋ ስጋት እንደሆነች በምትገልጻት ኢራን ላይ በፈጸመችው “ቀድሞ የመከላከል” ጥቃት (preemptive strike) የኻሚኒ ቢሮና በርካታ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ መጠነሰፊ የአየር ድብደባ አድርሳለች።

በኻሚኒ ቢሮ ላይ ብቻ 30 ከፍተኛ ፍንዳታ ያስከተሉ ቦምቦች ተጥለዋል።

እስራኤል ጥቃት ከጀመረች በኋላ “ትልቅ የውጊያ ዘመቻ” ውስጥ መግባታቸውን ያስታወቁት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ግባቸው እስከሚሳካ ድረስ ጥቃቱ ሳይቋረጥ ለሳምንት ይቀጥላል ብለዋል።

የኢራን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከሆነ በዚህ ጥቃት በሀገሪቱ 24 ግዛቶች ተማሪዎችን ጨምሮ 201 ሰዎች ተገድለዋል።

በሀገሪቱ ኻሚኒን ለማሰብ ለ 40 ቀናት የሚቆይ የሀዘን ቀን ታውጇል።

ኢራን እስራኤልንና የአሜሪካ የጦር ሰፈር ያለባቸውን የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን በሚሳይል በመምታት አጸፋ እየሰጠች ነው።

ቻይና፣ ሩሲያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ የተወሰኑ ሀገራት እስራኤልና አሜሪካ እየፈጸሙ ያሉትን  ጥቃቱ ሲያወግዙ አብዛኞቹ ደግሞ ግጭቱ እንደሚያሳስባቸው መግለጫ እያሰጡ ናቸው።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው