የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በእስራኤልና በአሜሪካ የተቀናጀ የአየር ድብደባ መገደላቸው መረጋገጡንና አስከሬናቸው መገኘቱን ሮይተርስ የእስራኤል ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል።
ኻሚኒ መቼ እና በምን ሁኔታ እንደተገደሉ ዘገባው ዝርዘር መረጃ አላቀረበም።
ነገርግን ቅዳሜ ጠዋት በተፈጸመው ጥቃት 30 ቦምቦች በኻሚኒ ቢሮና በሌሎች ወታደራዊ ኢላማቸዎች ላይ ተጥለው ከፍተኛ ፍንዳታዎች አስከትለዋል።
ስለጉዳዩ ኢራን እስካሁን ያለችው ነገር የለም።

እስራኤልና አሜሪካ በቴህራን ላይ ጥቃት የፈጸሙት ኢራን በኑክሌር መርሃግብሯ ላይ ከአሜሪካ ስታደርግ የነበረው ድርድር ፍሬ ባለማፍራቱ ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቴህራን ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ ኢራን መጥሮ እጣ ይገጥማታል የሚል ማስጠንቀቂያ አሰምተው ነበር።
ትራምፕ ከጥቃቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ የኢራንን የኑክሌር ጦር ለማውደም ታላቅ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ብለዋል። ኑክሌር የታጠቀች ኢራን ለህልውናቸው ስጋት እንደምትሆን የሚገልጹት እስራኤልና አሜሪካ፣ ኑክሌር ለመታጠቅ የሚያስላትን አቅም ማድቀቅ እንደሚፈልጉ ገለጸዋል።
አልጀዚራ እንደዘገበው በጥቃቱ 210 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች 747 የሚሆኑ ቆስለዋል።
ኢራን በበኩላ ወደ እስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ወደሚገኙባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚሳይል ናዳ በማዝነብ ነወሰ የአጸፋ ምላሽ የሰጠችው።
ኢራን በኳታር፣ በአረብ ኢምሬትስ፣ በባህሬንና በሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ የጦር ሰፈሮችን በማጥቃት፣ ግጭቱ ሰፊ ቀጣና እንዲሸፍን አድርጋዋለች።
ሩሲያና ቻይና፣ በኢራን ላይ የተቃጣውን ጥቃት በጽኑ በማውገዝ ቀዳሚ ሲሆኑ በርካታ ሀገራት ደግሞ ግጭቱ የበለጠ ቀጣናዊ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።











