Loading...

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ገቡ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስያ አህጉር ዋነኛ የዋሽንግተን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተቀናቃኝ ወደሆነችው ቻይና በዛሬው እለት ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ቻይና ያቀኑት ከአጋራቸው እስራኤል ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ የከፈቱትና መካከለኛው ምስራቅን ያመሰው ጦርነት ዘላቂ መፍትሔ ባላገኘበት ወቅት ነው።

በጦርነቱ ምክንያት ወሳኝ የሆነው የነዳጅ መተላለፊያ የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ፣ ቻይናም የችግሩ ተጠቂ እንድትሆን አድርጓታል።

በቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ግብዣ ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ቻይና ያቀኑት ትራምፕ ወይይት ከሚያደርጉባቸው ጉዳዮች አንዱ ኢራን ጦርነት እንደሆነ ተገልጿ።

ይሁን እንጂ ትራምፕ ከኢራን ጋር እያካሄዱ ያለውን ጦርነት ለማስቆም የቻይናን ድጋፍ እንደማይፈልጉ ከጉብኝቱ ቀደም ብለው ተናግረዋል።

እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ ከሆነ ሁለቱ መሪዎች  የቻይናና የአሜሪካ ግንኙነትን በተመለከቱ ዋናዋና ጉዳዮች እንዲሁም በአለም ሰላምና ልማት ላይ በጥልቀት ይወያያሉ። ሁለቱ መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እአአ በ2025 በኮሪያ ቡሳን ነበር። ይህ ጉብኝት በዘጠኝ አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ፕሬዝደንት የተደረገ የቻይና ጉብኝት ነው

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው