Loading...

የኢራንና አሜሪካ ፕሬዝደንቶች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ፈረሙ

ኢራንና አሜሪካ ፕሬዝደንቶቻቸው የፈረሙበትን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት በዛሬው እለት ይፋ ያደረጉ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ባለስልጣናት ስምምነቱን የማያከብሩ ከሆነ ማጥቃት እንደሚጀምሩ አስጠንቅቀዋል።

በፈረንሳይ ከሌሎች ኃያላን መሪዎች ጋር እየተወያዩ ያሉት ትራምፕ ኢራን የባለስቲክ ሚሳይል መታጠቅ የለባትም የሚለውንና ወደ ጦርነት የገቡበትን አንደኛውን ምክንያት “ኢፍትሃዊ” ነው በማለት ትተውታል።

ትራምፕ ኢራንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የኢራን መሪዎች “ስምምነቱን የማያከብሩ ከሆነ ከፍተኛ ድብደባ” እንደሚያደርሱ ዝተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው ይህ የ60 ቀናት ስምምነት፣ ጦርነቱ እንዲቆምና ተዘግቶ የነበረው ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲከፈት የሚያስችል ሲሆን ኢራን ኑክሌርና ዘላቂ የተኩስ አቁም ጉዳዮች ቀጣይ ድርድሮች ይካሄዱባቸዋል ተብሏል

የኢራን መሪዎች ለትራምፕ ማስፈራሪያ ምላሽ አልሰጡም። የኢራን ባለስልጣናት  እአአ ከ1979 ወዲህ የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝደንቶች የፈረሙበትን ሰነድ መልቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል

የኢራን ዋና ተደራዳሪ ሞሀመድ ባቃር ቋሊባፍ በወታደራዊ ኃይል ማሳካት ከምንፈልገው በብዙ እጥፍ የበለጠ በድርድሩ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ የነበረው በቢሊዮን የሚቆጠረው የኢራን ሀብት እንዲለቀቅ ከስምምነት መደረሱ ለኢራን ወሳኝ ከሆኑት የድርድሩ ውጤቶች አንዱ ነው።

ባለፈው የካቲት ወር፣ እስራኤልና አሜሪካ በመቀናጀት በኢራን ላይ ባካሄዱት ጦርነት፣ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለዋል ።ኢራን በአጸፋ በእስራኤልና የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ ጥቃት በመሰንዘሯ፣ ጦርነቱ ቀጣናዊ አለምአቀፋዊ ቀውስ እንዲያስከትል አድርጎታል።
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በመዝጋቷ ፣ አለምአቀፍ የነዳጅ አቅርቦት እንዲዛባና ዋጋ እንዲንር ምክንያት ሆኖ ነበር። ስምምነቱን ተከትሎ አለምአቀፍ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው