Loading...

አሜሪካ “ግትር አቋም” ባላቸው የህወሓት አባላትና ቤተሰቦቻቸው ላይ ማዕቀብ ጣለች

የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ሰላም እንዳይጸና እንቅፋት ሆነዋል ባለቻቸው ወግአጥባቂ (hardliner ) የህወሓት አባላትና በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የጉዞ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቋል

መግለጫው የአሜሪካ የቪዛ እገዳ ፖሊሲ ኢላማ የሚያደርገው “በትግራይ ያለው ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ እንዳያገኝ ባደረጉ እና በተባበሩ አካላት ላይ ነው” ብሏል

በህወሃትና በፌደራል መንግስት መካከል ያለው ውጥረት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ የጦርነት ስጋት መፍጠሩንና በቀጣናው ያለውን ሰላም ችግር ውስጥ መክተቱን የገለጸው መግለጫው፣ የትግራይ የጸጥታ ኃይሎችና የፌደራል መንግስት መከላከያ ሰራዊት በዚህ አመት መጀመሪያ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ጠቅሷል።

የአሜሪካ በክልሉ ያለውን ሰላምና መረጋጋት በሚያናጉ የትግራይና ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ ሁለንም አማራጮች እንደምትጠቀም መግለጫ አስጠንቅቋል።

አሜሪካ፣ በጥቅምት 2013 ዓ.ም የተጀመረውንና ለሁለት አመታተ የቆየውን ደምአፋሳሽ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያስቀመው የፕሪቶሪያው የዘላቂ ሰላም ስምምነት እንዲፈርም ጫና ማድጓ ይታወሳል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው