ግዛቷን በመውረርና በግጭት በተጎዳው ትግራይ ክልል ውስጥ ወታደሮቿን አስማርታለች የሚል ክስ በጎረቤቷ ኤርትራ ላይ ክስ ያቀረበችው ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ለተባበሩት መንግስታት(ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት አሳውቃለች።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጥቅምት መስከረም 28 በተጻፈ ደብዳቤ ኤርትራን በተደጋጋሚ ወታደራዊ ወረራ ፈጽማለች በሚል ከሰው፣ ኃይሎቿን ወዲያውኑ ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ ኤርትራ በድንበሩ አካባቢ ያላትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማጠናከሯንና የሜካናይዝድ ጦር ክፍሎችን ወደ ትግራይ ማስገባቷን ገልጸዋል። ይህም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ላይ ቀጥተኛ ስጋት እንደሚደቅን አስጠንቅቀዋል።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የማይወጣ ከሆነ አዲስ አበባ “ራሷን ከኤርትራ ከመከላከል ሌላ አማራጭ አይኖራትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት የጸጥታ ምክር ቤቱ እንዲመለከተው ጠይቃለች። የኤርትራ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በክልሉ ሰላምና ደኅንነት ላይ ስጋት እንደሚፈጥሩም አስጠንቅቃለች።
ኤርትራ በበኩሏ የኢትዮጵያን ክሶች ውድቅ በማድረግ፣ ክሶቹ በግዛቷ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ሰበብ የቀረቡ ናቸው ብላለች።
ይህ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጦር ከሕወሓት (TPLF) ኃይሎች ጋር በትግራይ ክልል ውስጥ እየተዋጋ ባለበት ወቅት የመጣ ነው።
ከክልሉ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ድሮኖች በአዲግራት አቅራቢያ የኤርትራ ወታደሮችን ይዘዋል በተባሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ሆኖም፣ ስለ ጥቃቱና ስለ ደረሰው የሰው ሕይወት ጉዳት የቀረቡት ሪፖርቶች በገለልተኛ ወገን እስካሁን አልተረጋገጡም።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ2020 እስከ 2022 በተካሄደው የትግራይ ጦርነት ወቅት በጋራ ተዋግተው የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግንኙነታቸው በእጅጉ ተበላሽቷል። ሁለቱም መንግሥታት ሌላው የክልሉን መረጋጋት እየደፈረ ነው በሚል ይከሳሉ።
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ወደብ ለማግኘት እያደረገች ያለው ጥረት፣ በተለይም የኤርትራን የዓሰብ ወደብ በተመለከተ ያላት ፍላጎት፣ ውጥረቱን የበለጠ አባብሶታል። ኤርትራ በበኩሏ የዓሰብ ወደብ የሉዓላዊ ግዛቷ አካል መሆኑን ትገልጻለች።
ኤርትራና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በይፋ ያቋረጡ ሲሆን ወደ አጠቀላይ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል።












