በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በግንባታ ላይ የነበረ ባለ 12 ፎቅ ሕንፃ በትናንትናው እለት መደርመሱ ተዘግቧል።
በፍርስራሹ ስር ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ስጋት መፈጠሩንና የነፍስ አድን ዘመቻ መጀመሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
የናይሮቢ ካውንቲ አስተዳደር በሰጠው መግለጫ በሕንፃው ፍርስራሽ ሥር ሰዎች መኖራቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች መውጣታቸውን አስታውቋል። ህንጻው በምን ምክንያት ሊደረመስ እንደቻለና አጠቃላይ የጉዳቱ መጠን እስካሁን አልታወቀም።
የናይሮቢ ከንቲባ ጆንሰን ሳካጃ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ በኢስትሌይ ሰፈር የሚገኘውና የተደረመሰው ይህ ህንጻ የመጀመሪያው ወለሉ(Ground floor) አገልግሎት እየሰጠ ነበር ብሏል።
ሮይተርስ የለቀቀው ቪዲዮ አደጋው በደረሰበት አካባቢ ሰዎች ተሰባስበውና ፍርስራሽ የማንሳት ቁፋሮ ሲካሄድ ያሳያል።










