Loading...

ትራምፕ ጦራቸውን በናይጄሪያ ላይ ለማዝመት በተጠንቀቅ ላይ እንደሆኑ ተናገሩ

Afro Insight News – የናይጄሪያ መንግስት ክርስቲያኖች እንዲገደሉ ፈቅዷል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ወንጅለዋል። በትሩዝ ሶሻል የማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የአሜሪካ ጦር ክፍል ለጦርነት በተጠንቀቅ እንዲብቅ ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ በማለት ቀጥተኛ ማስፈራሪያቸውን አሰምተዋል። “ ምላሻችን በጣም ፈጣን፥ ከባድ እና ጣፋጭ ይሆናል” ብለዋል፥ ትራምፕ በመግለጫቸው። ከጦር ማስፈራሪያው በተጨማሪ አሜሪካ ለናይጄሪያ የምታቀርበውን እርዳታ እንደምታቋርጥ ተናግረዋል።

ናይጄሪያ የትርምፕን ውንጀላ አጣጥላለች። ክርስቲያኖች ላይ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል የሚለው የዘር ማጥፋት ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ያሉት የናይጄሪያ ባለስልጣናት ግድያዎቹ ክርስቲያን እና ሙስሊም ሳይለዩ የተፈፀሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። “የግድያዎቹ ምክንያት ግን የጎሳ ቅራኔዎች፥ የመሬት ባለቤትነት ግጭቶች እና የአይር ንብረት ችግሮች ናቸው” ብለዋል። “የአገሬን ሁኔታ ያልተረዳ ሰው የሚያቀርበው ውንጀላ አገራዊ አንድነታችንን ሊያበላሽ ይችላል” ሲሉም ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

👉 ለተጨማሪ የአፍሪካና የዓለም መረጃዎች የአፍሮ ኢንሳይት ገፆችን ይከተሉ Afro-Insight News

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው