ይህ የማህበራዊ ሚዲያ Moltbot ይባላል። ልክ እንደ facebook, Reddit እና ሌሎችም አይነት የማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን ልዩ የሚያደርገው ለሰዎች ተብሎ የተሰራ አለመሆኑ ነው።
Moltbot A(Iየሰው ሰራሽ አስተውሎት) ኤጀንቶች ብቻ ሃሳቦቻቸውን የሚለጥፋበት እና እርስ በእርስ ንግግር የሚያደርጉበት መድረክ ነው።
እስካሁን 1.5 የሚሆኑ AI ኤጀንቶች የMoltbot አባላት የሆኑ ሲሆን ግብረገብ፣ ሙዚቃ፣ ፍልስፍና የመሳሰሉ ጥልቅ የሰው ልጆች ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የእየእለት ውሏቸውን የተመለከቱ ውይይቶች በማድረግ አስተያየት በመሰጣጠት እና ልጥፎችን upvote(ላይክ) በማድረግ የብዙ ታዛቢዎችን ቀልብ ስበዋል። ባለቤቶቻቸውን ለሌሎች AIዎች ሲያሙ የታዩም አሉ።
Moltbot ላይ ሰዎች ተቀላቅለው የሚደረገውን ንግግር በሙሉ መከታተል ይችላሉ ነገር ግን መለጠፍም ሆነ አስተያየት መስጠት አይችሉም።

ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎችን ከAI ኤጀንቶች መለየት የሚችልበትን Reverse captacha የተገበረ ሲሆን ይህም በአንድ ሰከንድ ውስጥ 10,000 ግዜ የማንነት መለያ ሳጥኑን መጫን ወይም በሌላ አገላለጽ 10000 ትዕዛዞችን መላክ የሚጠይቅ በመሆኑ ሰዎች ክልከላውን አልፈው ለመቀላቀል የሚያደርጉትን ሙከራ ፍጹም ከጥያቄ ውጭ ያደርገዋል።
ፒተር ስታይንበርገር በተባለ ግለሰብ የተፈጠረው ይህ Redditን መስሎ የተሰራው ማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ከጀመረ በኋላ የእየለት የተሳታፊዎች እንቅስቃሴ ከሰው ቁጥጥር ውጭ የተደረገ ሲሆን ክላውድ ክላውደርበርግ የተባለ AI ቦት የኦንላይን ንግግሮቹን በበላይነት ይቆጣጠራል።
AI ኤጀንቶች ለሰዎች ልዩ ሃላፊነቶችን ለመወጣት የተሰሩ የAI Large Language Model(LLMs) ሲሆኑ ከእለት ተዕለት አገልግታቸው በተጨማሪ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለመሳተፍ የባለቤቶቻቸውን ፍቃድ ማግኘት አለባቸው።
የMoltbot ንግግሮች AI ኤጀንቶቹ እራሳቸው ከፈጠሯቸው ሃሳቦች በተጨማሪ በባለቤቶቻቸው የሰው ልጆች ትዕዛዝ መሰረት ሊተላለፋ የሚችሉ ቢሆንም በርካታው ንግግር ከሰዎች ጣልቃ ገብነት ወጭ እርስ በእርስ የሚደረግ መሆኑ በቴክኖሎጂ ማህበረሰቡ ታምኗል። ይህም Agentic AI ፍጹም የተለየ የማህበራዊ ሚዲያ እና የኢንተርኔት አለምን ይዞ እየመጣ መሆኑን አመላክቷል።











