Loading...

የፌደራል መንግስት መቀሌን መልሶ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት መመለሱ ተገለጸ

የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱን እና ከሳምንት በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦች መገናኘታቸውን ቲክቫህ የተባለው የቴሌግራም ቻናል ዘግቧል።

በከተማዋ ኢንተርኔት የተቋረጠው፣ በክልሉ ገዥ ፓርቲ ህወሃትና በፌደራል መንግስት መካከል በ2013 ዓ.ም. ከተቀሰቀሰ የሁለት ዓመት ደምአፋሳሽ ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሳምንት ወደ ጦርነት መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

እንደ ቲክቫህ ዘገባ በአሁኑ ወቅት ከፌደራል መንግስት ጎን ሆነው እየተዋጉ የሚገኙት “የትግራይ የሰላም ኃይል” የሚባሉት ታጣቂዎች የመቀሌ 104.4 ኤፍኤምን ተቆጣጥረው “ከተማውን የሚያረጋጉ መልእክቶችን እያስተላለፉ” ነው።

በጦርነቱ የፌደራል መንግስት ጦር መቀሌን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ከህወሓት ይዞ ነጻ ማድረጉንና ህወሃት ማፈግፈጉን ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ ግጭት ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ ቀንድና የባህረ ሰላጤ ሀገራትን ሊያሳትፍ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ኤርትራ፣ ግብጽና ሱዳን በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን እየደገፉ ነው ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲውን በመዝጋትና 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ከአዲስ አበባ በማባረር፣ ከኤርትራ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጧል። ኤርትራም በምላሹ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን “ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት” ማቋረጧን መግለጿ ይታወሳል። ኤርትራ፣ ግብጽና የደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ግጭት እጃቸው እንደሌለበት አስተባብለዋል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው