Loading...

በአሜሪካ፣ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንደ ስማርት ስልክ ቻርጅ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሃይዌይ ላይ ተግባራዊ ሆነ

ይህ ሩብ ማይል ርዝመት ባላው መንገድ ክፍል ላይ የተገጠመ ቴክኖሎጂ፣ የመጀመሪያው የሃይዌይ መኪና በእንቅስቀሴ ላይ እንዳለ ቻርጅ ማድረግ ችሏል። ቴክኖሎጂው የተተገበረው በኢንዲያና፥ አሜሪካ ውስጥ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ተግባራዊ ከሆኑት ለየት የሚያደርገው ከባድ መኪናን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ኢቪ መኪኖችን በስኬት ቻርጅ ማድረግ መቻሉ እንደሆነ ተገልጿል።

የፐርዱ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት ይህ ገመድ አልባ ቻርጀር ቴክኖሎጂ፣ ከመንገዶች አስፓልት ንጣፍ ስር ተዘርግቶ፣ በማግኔቲክ ፊልድ አስተላላፊ መኪኖች በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ሃይል ይሞላል።

በፓድ ቻርጅ እንደሚያደርጉ ስማርት ስልኮች፥ ቻርጅ ማድረጊያው እና የኤሌክትሪክ መኪናው ሃይል መቀበያ የኮፐር ገመዶች ትይዩ ሆነው በኢንዳክቲቭ ቻርጂንግ ወደ መኪናው የኤሌክትሪክ ሃይል ይተላለፋል።

የመንገዱ አገልግሎት ሙከራ ላይ አንድ ከባድ መኪና በስኬት ቻርጅ ማድረግ የተቻለ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልጸው፥ እስካሁን ድረስ ቴክኖሎጂው ያለበት ብቸኛ ውስንነት የሃይል ፍጆታው ከፍተኛ መሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። ለምሳሌ በሰዓት 65 ኪ/ሜ እየተጓዘ ያለ ከባድ መኪና ቻርጅ ለማድረግ የሚያስፈልገው ሃይል መጠን(200ኬሎ ዋት) ለአራት መኖሪያ ቤቶች የሚያገለግል ሃይል ፍጆታን የሚጠይቅ መሆኑ ይናገራሉ።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው