Loading...

ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ግብጽና ሶማሊያ በቀይ ባህር አስተዳደር ጉዳይ የጋራ አቋም መግለጫ አወጡ

Eritrea Severs Diplomatic Ties with Ethiopia in Tit-for-Tat Measure

ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ግብጽና ሶማሊያ በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ አስተናጋጅነት በኤል አላሜይን ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ ቀይ ባህርን ማስተዳደር የሚችሉት የቀይ ባህር ዳርቻ ሀገራት (littoral countries) ናቸው ብለዋል።
ሀገራቱ በመግለጫቸው ከሶማሊላንድ ጋር በተያያዘ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለመጣስ የሚደረገውን ጥረትና በሱዳን ጉዳይ እየታየ ያለውን የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ተቃውመዋል።
ይህ ስብሰባ የተካሄደው በሰሜን ኢትዮጵያ ድጋሚ ግጭት ባገረሸበትና የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራ፣ ሱዳንና ግብጽን የሀገር ውስጥ ታጣቂዎችን እያስታጠቁ ነው የሚል ክስ እያቀረበ ባለበት ወቅት ነው። እነዚህ ሀገራት የቀረበባቸውን ክስ በተደጋጋሚ አስተባብለዋል።
ግጭቱ ባለፈው መስከረም 13፣ 2019 ዓ.ም. በይፋ ከተቀሰቀሰ በኋላ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራና ግብጽ ላይ ተከታታይ የዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችን ወስዷል። በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲውን በመዝጋትና 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በማድረግ፣ እንዲሁም አንድ ግብጻዊ ዲፕሎማትን በማባረር፣ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን ከፍተኛ ደረጃ አድርሶታል። ይህን ተከትሎ ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉንም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠች ሲሆን፣ ግብጽ ደግሞ አንድ በግብጽ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረባ በማባረር የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች።
ይህ ግጭት የአፍሪካ ቀንድና የአረብ ባሕረ ሰላጤ ሀገራትን ሊያሳትፍ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ቀውስ መሸከም አይችልም ያላቸው አሜሪካ፣ ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ አሳስባለች።
ኢትዮጵያና ሶማሊያም ቢሆኑ ከሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት ጋር በተያያዘ ግንኙነታቸው ሻክሮ ነበር። ከሁለት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለማግኘትና በምትኩ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሟ፣ ሶማሊላንድን የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያትን ሶማሊያን በእጅጉ አስቆጥቷት ነበር። በዚህ ምክንያት ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር በማባረር ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ ይታወሳል።
ቱርክ በሁለቱ ሀገራት መካከል ነግሦ የነበረውን ውጥረት ለማለዘብ ባደረገችው ጥረት፣ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እንድታከብር፣ እንዲሁም ሶማሊያ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደብ የምትጠቀምበትን መንገድ እንድታመቻች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው