Loading...

ኢትዮጵያዊውን ከ89 አመታት በፊት የከፈሉት መስዋእት ምን ያህል መራር ነበር?

ከዛሬ 89 አመት በፊት በየካቲት 12፣ 1937 ዓ.ም  አብራሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያዊውን በያኔው ገነተ ልኡል ቤተመንግሥት ወይም በዛሬው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ በተካሄድ የአደባባይ ዝግጅት ላይ ቦምብ ወረወሩ። ቦምቡ ኢላማ ያደረገው በጣሊያኑን ወራሪ ጦር መሪ ሮዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ነበር። ግራዚያኒ ግን ቆስሎ ተረፈ።

ምንም እንኳን ግራዚያኒ ከሞት ቢተርፍም የጣሊያን ኃይል በበቀል ተነሳስቶ በኢትዮጵያውያን ላይ ለሶስት ቀናት የፈጀ የዘር ጭፍጨፋ ማካሄዱን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በጠብመንጃ፣ በቢላ፣ በመጥረቢያ እንዲሁም ቤቶችን ዘግቶ በማቃጠል በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በዘግናኝ ሁኔታ ገድሏል።

በጥቃቱ በአዲስ አበባ ብቻ 30000 ሺ ገደማ ሰዎች ተገድለዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ደግሞ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመቶዎች የሚቆጠሩ መነኮሳት የተገደሉበት ቦታ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህን ጭፍጨፋ ለማስታወስ ጣሊያን ተሸንፎ ከወጣ በኋላ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ በስድስት ኪሎ 28 ሜትር ርዝመት ያለው “የሰማዕታት ሀውልት” አሰርተው ታህሳስ 5፣ 1948 አስመርቀዋል።

የተጨፈጨፉ ሰማዕታትን ለማሰብ በየአመቱ የካቲት 12 ታስቦ ይውላል። እለቱ እንደ ብሔራዊ በዓል ባይከበርም የመንግስት ባለስልጣናትና የጥንታዊት ኢትዮጵያዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሰማዕታትን ያስባሉ።

ይህንን መራር መስዋዕትነት ለማስታወስ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ በ1948 ዓ.ም በስድስት ኪሎ 28 ሜትር ርዝመት ያለው የሰማዕታት ሐውልት አሰርተዋል። በዛሬው መታሰቢያ ላይ የተገኙት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን “ትውልዱ አያትና ቅድመ አያቶቹ የከፈሉትን መስዋዕትነት ሊዘነጋው አይገባም” ሲሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያውያን በዱር በገደል ለአምስት ዓመታት ባደረጉት ተጋድሎ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ፋሽስት ጣሊያንን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፈው ነጻነታቸውን ተቀዳጅተዋል። ዛሬ 100ኛ ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን የምታከብረው ጣሊያን እና ኢትዮጵያ በወቅቱ የነበረውን ቁስል በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጠገን ጥረት ማድረጋቸው ይታወሳል።

እለቱ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ስልጣን እስከያዘበት 1967 ዓ.ም ድርስ ብሔራዊ በሔራዊ በዓል ነበር።

በጣሊያን የግፍ አገዛዝ የተማረሩ ኢትዮጵያዊያን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀችውን ጣሊያንን ለአምስት አመታት በዱርና በገደል ከተፋለሙ በኋላ ሚያዝያ 27፣1933 ጣሊያንን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ ጽፈዋል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው