Loading...

ኢራን የተጠቀመችው ‘ክላስተር’ ሚሳኤል ለምን ዓለምን አስፈራ?

ዛሬ ቅዳሜ በሰባት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ የተተኮሰው የኢራን ክላስተር ባሊስቲክ ሚሳኤል ተራ የሚሳኤል ጥቃት ሳይሆን በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ቦምቦችን የመርጨት አቅም ያለው አውዳሚ መሣሪያ ነው።

የክላስተር ሚሳኤል የቴክኖሎጂ ሚስጥር

አንድ ክላስተር ሚሳኤል በውስጡ በርካታ ትናንሽ ቦምቦችን (Submunitions) ይይዛል። ሚሳኤሉ ኢላማው ላይ ከመድረሱ በፊት አየር ላይ ይከፈትና እነዚህን ቦምቦች እንደ ዝናብ ይረጫቸዋል።

ዛሬ ኢራን የተጠቀመችው ሚሳኤል በእያንዳንዱ ራስ ላይ 20 ትናንሽ ቦምቦችን አዝሎ እንደሚበር ተነግሯል።

እንደ አይረን ዶም (Iron Dome) ያሉ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች አንድን ሚሳኤል አየር ላይ መትቶ ለማውረድ የተሰሩ ናቸው። ነገር ግን አንድ ሚሳኤል ተከፍቶ 20 ቦምቦች ሲሆኑ የመከላከያ ሥርዓቱ የትኛውን መምታት እንዳለበት ግራ እንዲጋባና አንዳንድ ቦምቦች መሬት እንዲነኩ ዕድል ይሰጣል።

አንድ መደበኛ ሚሳኤል አንድን ሕንፃ ወይም የተወሰነ ቦታ ብቻ ነው የሚያፈርሰው። ክላስተር ሚሳኤል ግን እስከ 8 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ስፋት ላይ ቦምቦችን ስለሚበትን ሰፊ የመኖሪያ መንደሮችን፣ የጦር ሰፈሮችን እና የኤርፖርት መሮጫ መንገዶችን በአንድ ጊዜ ከጥቅም ውጭ ያደርጋል።

ክላስተር ቦምቦች ጦርነቱ ካበቃ በኋላም ሳይፈነዱ መሬት ላይ ተቀብረው ስለሚቀሩና ንጹሃን ዜጎችን ስለሚገድሉ በዓለም አቀፍ ስምምነት (Convention on Cluster Munitions) አጠቃቀማቸው የተገደበ ነው።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው