Loading...

ሜሲ ሃትሪክ በመስራት በአለምዋንጫ ታሪክ ከፍተኛ ግብ ካስቆጠረው ክሎዝ ጋር እኩል ሆነ

ሜሲ ሐት-ትሪክ በመሥራት የክሎዝን እና የሮናልዶን ታላላቅ ክብረ-ወሰኖች በአንድ ሌሊት ሰበረ!

አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ኮከብ ሊዮነል መሲ ትናንት ሀገሩ አርጀንቲና ከአፍሪካዊቷ አልጀሪያ ጋር ባደረገችው የ2026ቱ የአለምዋንጫ ጨዋታ ሶስት ግብ (ሃትሪክ) በመስራት በዓለምዋንጫ ታሪክ ከፍተኛ ግብ ካስቆጠረው ጀርመናዊ ሚሮስላቭ ክሎዝ ጋር እኩል ሆኗል

ለሀገሩ ለ200ኛ ጊዜ የተሰለፈው ሜሲ በዚህ የአለምዋንጫ የመጀመሪያውን ሃትሪክ በመስራት ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።  የስምንት ጊዜ ባላንዶር (Ballon d’Or) አሸናፊው ሜሲ፣ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ክሎዝ ጋር እኩል 16 ግቦችን በማስቆጠር እኩል ሆኗል።

በስድስት የአለምዋንጫ ውድድሮች በመሰለፍ የመጀመሪያ የሆነው ሜ በመጀመሪያ አጋማሽ ላይ በአልጄሪያው አይሳ ማንዲ ላይ በሰራው ግዴለሽ ጥፋት ባለመቀጣቱ እድለኛ ነው ሲል ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።

በቡድን “J” ውስጥ የተደለደለውና ውድድሩን በድል የጀመረው የአርጄንቲና ቡድን፣ በቀጣይ ከጆርዳንና ከኦስትሪያ ጋር ይጋጠማል።

ሜሲ የ39ኛ አመት ልደቱን ካከበረ ከሳምንት በኋላ ባሳየው አስገራሚ ብቃት ሀትሪክ የሰራ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመሆን በረጅም ጊዜ ተቀናቃኙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን(Record) ነጥቋል።

ሜሲ በአለምአቀፍ ጨዋታ ለመቆየት መወሰኑ ከአራት አመት በፊት አርጀንቲና የኳታሩን የአለም ዋንጫ እንድታነሳ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ታሪኮች ተሰርተዋል። ይህ አፈጻጸሙ ግን ሜሲ በአሜሪካው ሚያሚ ክለብ ለመጫወት የወሰነው፣ አርጀንቲና የአለምዋንጫን ለአራተኛ ጊዜ እድታነሳ ለመርዳታ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው