በኔፓልናቲቤት ድንበር ላይ በተከሰተው ከባድና ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 389 የደረሰ ሲሆን ከ900 በላይ ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።
የነፍስ አድን ሰራተኞች በህይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት በጥድፊያ ላይ ናቸው። አደጋው ቤቶችን በመደርመስ፣ ዝቅተኛ ቦታ ያሉ መንገዶችን በማጥለቅለቅና ድልድዮችን ጠራርጎ በመውሰድ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
ቢቢሲ የኔፓል ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ይህ ከባድ የጎርፉ አደጋ ሊከሰት የቻለው በሂማሊያ ተራራ ጀርባ ያለው የበረዶ ክምር በመናዱ ምክንያት ነው ብለዋል።
በአደጋው ከሀገሪቱ ዜጎች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተዘግቧል።












