Loading...

ናይጀሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 100 ህጻናት ተማሪዎችን ማስለቀቋ ተዘገበ

የናይጄሪያ መንግስት ባለፈው ወር ኒጀር ከተባለ ግዛት በጅምላ ታግተው የተወሰዱ 100 ህጻናት ተማሪዎችን ማስለለቁን ሮይተርስ የሀገሪቱን ቻነልስ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ ይህ እገታ በሀገሪቱ በታጣቂዎች በተደጋጋሚ ከተፈጸሙ አስከፊ የጅምላ እገታዎች አንዱ ነው።

የናይጀሪያ ክርስቲያን ማህበር(ካን) እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ታጣቂዎች በግዛቲቱ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳም ላይ በፈጸሙት ጥቃት የትምህርት ቤቱን 12 ሰራተኞች አግተው መውሰዳቸውን ገልጾ ነበር።

ጥቃቱ ከተፈጸመ ከተወሰነ ሰአታት በኋላ 5ዐ ተማሪዎች ማምለጣቸው የተነገረ ቢሆንም የትና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ አሁን ላይ መረጃ የለም። ተለቀዋል ስለተባሉት ተማሪዎች ጉዳይ የሀገሪቱ ሚዲያዎችም ዝርዝር መረጃ አላወጡም።

“በይፋ የምናውቀው ነገር የለም፣ የፌደራል መንግስትም በግልጽ አላሳወቀንም። ይህ እውነት እንዲሆንና ሌሎቹም እንዲለቀቁ እንጸልያለን” ሲሉ ዳንኤል አቶሪ በኒጀር ግዛት የሚገኘው ካን ኃላፊ ተናግረዋል።

ከችቦክ ልጃገረዶች እገታ ከ10 አመት በኋላ የተፈጸመው ይህ የጅምላ እገታ በአሜሪካ ጫናው ውስጥ የሚገኘቱ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ትኩረት እንዲያርፍባቸው አድርጓቸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ታጣቂዎች በሰሜናዊ ናይጀሪያ ክርስቲያኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየፈጸሙ ሲፈጽሙ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እርምጃ አልወሰዱም የሚል ከፍተኛ ትችት በቅርቡ ማሰማታቸው ይታወሳል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው