Loading...

ዩጋንዳ የስታርሊንክ ኢንተርኔት መሳሪያዎች እንዳይገቡ እገዳ ጣለች

የዩጋንዳ መንግስት ብሔራዊ ምርጫው ሊካሄድ ሳምንታት ሲቀሩት የስታርሊንክ ሳተላይት መሳሪያዎች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ እግድ መጣሉ ተዘግቧል።

መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ በድጋሚ የኢንተርኔት ገደብ ሊጣል ይቻላል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት ነው።

ከ43 አመቱ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ከነበረው ፖለቲከኛ ቦብ ዋይን ጋር የሚወዳደሩት የ81አመቱ ዩሪ ሙሴቬኒ በጥር አጋማሽ በሚካሄደው ምርጫ የስልጣን ዘመናቸውን ግማሽ ክፍለ ዘመን ለሚጠጋ ጊዜ ለማራዘም ይፈልጋሉ።

እ.ኤ.አ. በ2021 በተካሄደው ምርጫ መንግስት ለቀናት የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጦ ነበር። በምርጫው ከሙሴቬኒ በረጅም ርቀት ሁለተኛ ሆነው ሲመሩ የነበሩት ዋይን ምርጫው መጭበርበሩን በመጥቀስ ውጤቱን ውድቅ አድርገዋል። ሙሴቬኒ ግን ይህን ክስ አስተባብለዋል።

ወደ ዩጋንዳ በሚገቡ የስታርሊንክ መሳሪያዎች ላይ እግድ መጣሉን ከአራት ቀናት በፊት ሾልኮ የወጣ የታክስ ኤጀንሲ ማስታወሻ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው በመዘዋወሩ ነበር።

የሀገሪቱ የገቢዎች ባለስልጣን ቃል አቀባይ የዚህን ማስታወሻ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።

ይህ ማስታወሻ እንደሚለው ማንኛውንም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የስታርሊንክ ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች፣ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች እና ተያያዥ እቃዎች የሙሴቬኒ ልጅ በመሆነው የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ሙሆዚ ኬነሩጋባ መጣራት አለባቸው።

የገቢዎች ቢሮ ብዙ ሀገራት የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች መቆጣጠር ይፈልጋሉ በማለት የተጣለውን እገዳ አጣጥሎታል። የቢሊየነሩ ኢሎን መስክ የሆነው ስታርሊንክ በዩጋንዳ ለመስራት ፍቃድ ባይኖረውም ብዙ ዩጋንዳውያን እያስገቡ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በትክክለኛ ስማቸው ሮበርት ኪያጉላኒ እየተባሉ የሚጠሩት ዋይን በስታርሊንክ የተጣለውን እገዳ የማይረባ ሲሉ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።

“ምርጫውን ለማጭበርበር ካላቀዱ በምርጫው ሂደት ህዝብ ኢንተርኔት ቢያገኝ ለምን ይፈራሉ”ሲሉ ጽፈዋል።

የቀድሞ አማጺ የሆኑት ሙሴቬኒ ዩጋንዳን በማረጋጋት ፣ የኢኮኖሚ እድገት በማምጣት እና ኤችአይቪ ኤድስን በመዋጋት ሲወደሱ ተችዎቻቸው ደግሞ ተቃዋሚዎችን በማፈን፣ በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ስማቸውን ያነሳሉ።

ሙሴቬኒና መንግስታቸው የእድሜና የስልጣን ቆይታ ገደብን ለመሻር ሁለት ጊዜ ህገመንግስት አሻሽለዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው