Loading...

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የሰጠችውን ጊዜያዊ ከለላ ሟቆሟ ተዘገበ

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ ህጋዊት ሟቋረጡ ተዘግቧል።

የአሜሪካ ሆምላንድ ሴኩሪቲ ሴክሬታሪ ክሪስቲ ኖይም “የሀገሪቱ ሁኔታ ከተገመገመና ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በኋላ ጊዜያዊ ጥበቃ ለማግኘት የሚያስችል መስፈት” አያሟሉም የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የከለላ ፍቃድ የምትሰጠውም ሆነ የምታራዝመው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግጭቶች ሁኔታዎችን እንደ ምክንያት በመጥቀስ ነበር።

የኢትዮጵያን መንግስት በዚህ ወሳኔ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

እ.ኤ.አ. እስከ 2022 ድረስ ከ356ሺ በላይ በኢትዮጵያ የተወለዱ ወይም የኢትዮጵያን ዝርያ ላያቸው ሰዎች አሜሪካ ውስጥ እንደሚኖሩ የአሜሪካ ሴንሰስ ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው