Loading...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለጋዛ ጸጥታ ኢትዮጵያ ጦሯን እንድታዋጣ በአሜሪካ ጥያቄ እንደቀረበላቸው የእስራኤል የመረጃ ምንጭ ጠቁሟል

በጋዛ እንዲሰሚራ ለታቀደው አለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል አሜሪካ የኢትዮጵያን ሰራዊት ተሳትፎ ጠይቃለች ተብሏል
ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል በቅርቡ እንደዘገበው ሁኔታውን በቅርበት የሚያውቁ “ምዕራባውያን ዲፕሎማቶችን” የነገሩኝ ነው በማለት ባወጣው ዘገባ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሊ አዲስ ለታቀደው የጋዛ አለም አቀፍ የፀጥታ ሃይል ወታደሮች እንዲያበረክቱ መጠየቃቸውን አስነብቧል።

በዚህ ዘገባ መሰረት የኢትዮጵያ የታሰበው ተሳትፎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት ባለ 20 ነጥብ የጋዛ የጸጥታ እቅድ አካል ይሆናል። እቅዱ ለሁለት ዓመታት ከዘለቀው አውዳሚ ጦርነት በኋላ በጦርነቱ በእጅጉ የተጎዳችውን የፍልስጤም ግዛት መልሶ የመገንባት ሂደትን የሚቆጣጠር ዓለም አቀፍ የጦር ኃይል እንደሚሰማራ ይገልጻል።

በዓመቱ መዝግያ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአለም አቀፍ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፥ በጋዛ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊነት ገና በሂደት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ለታቀደው ተልእኮ የበጀት ጉዳይ፣ ሃማስ ቀላል የጦር መሳሪያ ይዞ ሊቀጥል መቻሉን በተመለከተ እና ለጸጥታ ተሳትፎ የሚያደርጉ አገራት የሚኖራቸው ስልጣንን ጨምሮ በርካታ ቁልፍ ጉዳዮች ያልተፈቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሩቢዮ በመቀጠል ፓኪስታን እስካሁን ጥያቄ ከቀረበላቸው አገራት ፍቃደኝነቷን የገለጸች የመጀመሪያዋ አገር መሆኗን ገልጸዋል። ሩቢዮ ለሌሎች አገራትም ጥያቄ እንደቀረበላቸው እና ምላሾችን እየጠበቁ እንደሆነ ተናግረዋል።
የዘታይምስ ኦፍ እስራዔል ዘገባም፥ ኢትዮጵያ ፍቃዷን የገለጸች ስለመሆኗ ያለው ነገር ባይኖርም በተልዕኮው ውስጥ ተሳትፎን ለማድረግ ጥያቄ እንደቀረበላት ከዚሁ ዜና ጋር አያይዞ ነበር የዘገበው።

እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2025 ግጭት ለማቆም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊነት ግን ጥያቄ ውስጥ ወድቋል። በስምምነቱ መሰረት እስራኤል ጋዛን ጥላ እንድትወጣ የሚጠበቅባት ሲሆን፣ በሃማስ ምትክ የግዛቱን ግዜያዊ አስተዳደር ስራ የአለም አቀፍ የጸጥታ ሃይላት ጥምረት ይወስዳል። በተጨማሪ የአለም አቀፍ የጸጥታ ሃይሉ የሚሰማራው ጋዛን ከወታደራዊ ቀጠናነት ነፃ የማውጣት ጥረቶችን ለመደገፍ ይሆናል። ሆኖም ስምምነቱ ከተደረሰ በሗላ እስራዔል የሃማስ መሪ የሆነን ግለሰብ መግደሏ እና ተጨማሪ ስምምነቱን የሚጥሱ እንቅስቃሴዎች ወደዚህ ምዕራፍ የሚደረገውን ግስጋሴ አዝጋሚ አድርገውታል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው