Loading...

በ2025 በዓለም ጠንካራ ፓስፖርት ያላቸው 10 ሀገራት

በ2025 በጣም ጠንካራ የሚባሉት ፓስፖርቶች አብዛኛዎቹ የአውሮፓና የእስያ ሀገራት መሆናቸውን ሄንሊይ ፓስፖርት ኢንዴክስ በቅርቡ ያወጣው መረጃ ደረጃ ያመለክታል።

ሄንሌይ ፓስፖርት ኢንዴክስ የፓስፖርቶችን ጥንካሬ ደረጃ የሚሰጠው ባለፓስፖርቶቹ በቅድሚያ ቪዛ ማስመታት ሳያስፈልጋቸው በሚጓዙባቸው መዳረሻዎች ቁጥር ነው። ኢንዴክሱ ከአለምአቀፍ የአየር ትንስፖርት ማህበር(አይኤቲኤ) ባገኘው መረጃ መሰረት 199 ፓስፖርቶችንና 277 መዳረሻዎችን ገምግሟል።

በጥንካሬው ከዓለም ቀዳሚው የሲንጋፖር ፓስፖርት

የሲንጋፖር ፓስፖርት ያለ ቅድመ ቪዛ ወደ 192 መዳረሻዎች ለመጓዝ የሚያስችል ጠንካራ ከሚባሉት ፓስፖርቶች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ነው። ይህ ሲንጋፖር ከሌሎች ሀገራት በቀዳሚነት እንድትቀመጥ ያደረጋት ሲሆን ሀገሪቱ ካላት ጠንካራ አለምአቀፍ ትብብርና ትስስር የመነጨ መሆኑን ያሳያል።

ከሲንጋፖር ቁጥሎ የደቡብ ኮሪያና የጃፓን ፓስፖርቶች ከእስያ፣ የቤልጂየም፣ የፈረንሳይ፣ የአየርላንድ፣ የጀርመን፣ የጣሊያንና የበርካታ ስካንዲናቪያንስ ሀገራት ፓስፖርቶች ከአውሮፓ በጥንካሬያቸው ወሳኝ የሚባሉ ደረጃዎችን ይዘዋል። አሜሪካ በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ብትበለጥም ከቀዳሚ 10 ሀገራት ውስጥ ነች።

የአየር በረራ ፍላጎት መጨመር

ይህ የፓስፖርት ጥንካሬ ደረጃ የወጣው አለምአቀፍ የአየር በረራ ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ባሻቀበበት ወቅት ነው። አይኤቲኤ ባለፈው ጥር ወር ባወጣው መረጃ መሰረት በ2025 የነበረው የአየር በረራ ፍላጎት ከ2024 ጋር ሲነጸጸር በ5.3 በመቶ የጨመረ ሲሆን ጠቅላላ አቅም ደግሞ በ5.2 በመቶ ከፍ ብሏል። የአየር በረራዎችም 83.6 በመቶ ሙሉ እንደነበሩ ይህም እስካሁን ከተመዘገቡት የሙሉ አመት በረራዎች ከፍተኛ እንደሆነ መረጃው ያመለክታል። አለምአቀፍ የበረራ ፍላጎት በፍጥነት አድጎ 7.1 በመቶ ደርሷል።

ያለ ቪዛ ወደ ብዙ መዳረሻዎች ለመጓዝ የሚያስችሉት 10 ጠንካራ ፓስፖርቶች የሚከተሉት ናቸው። (በደረጃ ከ1-10)

1.ሲንጋፖር(192 መዳረሻዎች)

2.ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን(187 መዳረሻዎች)

3.ስዊድን፣ አረብ ኢሚሬትስ(186 መዳረሻዎች)

4. ቤልጀም፣ ዴንማርክ፣ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣
ሉግዘንበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ኖርዌይ፣ስፔን እና ስዊዘርላንድ(185 መዳረሻዎች)

5.ኦስትሪያ፣ ግሪክ፣ ማልታ፣ፖርቹጋል(185 መዳረሻዎች)

6.ሀንጋሪ፣ ማሌዥያ፣ ኒውዝላንድ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫኪያ፣ስሎቬኒያ(183 መዳረሻዎች)

7.አውስትራሊያ፣ ክሮሺያ፣ ቼክ፣ ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ፣ዩናይትድ ኪንግደም(182 መዳረሻዎች)

8.ካናዳ፣ ሊችተንስቴን፣ሉቴኒያ(181 መዳረሻዎች)

9.አይስላንድ(180 መዳረሻዎች)

10. አሜሪካ(179 መዳረሻዎች)

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው