Loading...

ግርማ ዋቄ የኡጋንዳ አየርመንገድ ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

በአቬሽን ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ኢትዮጵያዊው ግርማ ዋቄ የኡጋንዳ አየርመንገድ አማካሪና ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ ጋዜጣ ሞኒተር ዘግቧል።

የግርማ ሹመት የጸደቀው በፕሬዝዳንት ዮዎሪ ሙሴቪኒ መሆኑንም ዘገባው ጠቅሷል።

አቶ ግርማ የተሾሙት የወቅቱን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀኒፈር ባሙቱራኪን መልቀቅ ተከትሎ የተፈጠረውን የአስተዳደር ክፍት እንዲሞሉ ታስቦ ነው።

ፕሬዝደንቱ ለትራንስፖርትና ስራዎች ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት በጻፉት ደብዳቤ ነበር ግርማ አማካሪና ግዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሾሙ የፈቀዱት።

“ግርማ ዋቄን አማካሪና ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ አድርገህ በመሾም በአየርመንዱ ውስጥ ያሉትን በርካታ ድክመቶች እንዲያስተካክል እንድታደርግ ፈቅጃለሁ። በተጨማሪም በሐምሌ 2026 አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ እስከምንሾም ድረስ ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኖ ያገለግላል” ሲሉ ፕሬዝደንቱ መናገራቸውን ጋዜጣው አስነብቧል።

ፕሬዝዳንቱ ተሰናባቿን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀኒፈር ባሙቱራኪን የሚተኩት አቶ ግርማ ከቦርዱ ጋር በቅርበት ይሰራሉ ብለዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው