Loading...

ወታደራዊ ክምችቱ በንግግሩ ላይ ጥላ በማጥላቱ ምክንያት አሜሪካና ኢራን ወደ ጦርነቱ እያመሩ ነው

አሜሪካና ኢራን በኢራን የኑክሌር መርሃግብር ዙሪያ ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ ከገቡ በርካታ አመታትን አስቆጥረዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ተስፋቸው እጨለመ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካና ኢራን በፍጥነት ወደ ጦርነት እያመሩ መሆናቸውን ሮይተርስ የሁለቱን ሀገራት ባለስልጣናትንና በአረብ ባህረሰላጤ ያሉ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የኢራን የአረብ ባህረሰላጤ ጎረቤቶችና እስራኤል ውጥረቱ ከስምምነት ይልቅ ወደ ጦርነት ሊያመራ ይችላል ብለው እንደሚያስቡ የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች ዋሽንግተን ኢራቅን ከወረረችበት እኤአ ከ2003 ወዲህ ግዙፍ ወታደራዊ ስምሪት አካሄዳለች ብለዋል።

ባለፈው ሰኔ ወር አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረሷ የሚታወስ ሲሆን በድጋሚ ጥቃት የሚፈጽሙ ከሆነ በአመት ለሁለተኛ ጊዜ ይሆናል።

የቀጣናው ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ ነዳጅ አምራች የሆኑት የባህረሰላጤው ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ግጭት ይፈጠራል የሚል ስጋት ውስጥ ስለገቡ ዝግጅት እያደረጉ ናቸው።
ሁለት የእስራኤል ባለስልጣናትን ለሮይተርስ እንደተናገሩት በቴህራንና ዋሽንግተን መካከል ያለው ልዩነት የማይጠገንና ወታደራዊ ውጥረት የመጨመር እድሉ የሰፋ ነው። ጥቂት የቀጣናው ባለስልጣናት እንደገለጹት ኢራን በቀጣናው ከፍተኛ ጦር እያከማቹ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስምምነት እንዲመጡ ጠጣር ጥያቄዎችን በማቅረብ የተሳሳተ ስሌት ውስጥ ገብታለች።

“ሁለቱም ወገኖች ከአቋማቸው ፈቅ አላሉም” ያሉት አላን እይሬ የተባሉት የቀድሞ የአሜሪካ ዲፕሎማት “አሜሪካና ኢራን ከቀይ መስመራቸው(ያደርጉታል ብየ ከማልጠብቀው) የማያፈገፉጉ ከሆነ” ትርጉም ያለው ነገር እንደማይመጣ አክለው ገልጸዋል።
“ትራምፕ ይህን ያህል ጦር አሰባስቦ፣ ትርጉም ያለው ስምምነት ላይ ሳይደረስ መመለስ አይችለም፤ እኔ የተዋረደ ያህል ይሰማዋል ብዩ አስባሉሁ” ብለዋል። “ጥቃት የሚሰነዝር ከሆነ ነገሩ አስቀያሚ ይሆናል።”

አሜሪካና ኢራን በዩራኒም ማበልጸግ፣ በማዕቀብና በሚሳይል ዙሪያ በሁለት ዙር  ያደረጓቸው ንግግሮች ቆመዋል። የኦማኑ አደራዳሪ የሚሳይል ጉዳይን የያዘውን የአሜሪካን ደብዳቤ ለኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሲሰጧቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለመክፈትም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ባለፈው ማክሰኞ በጄኔቫ ከተካሄደው ንግግር በኋላ ኢራን “በመመሪያ መርሆዎች” ላይ መስማማታቸውን ብትገልጽም ዋይትሀውስ ግን  በመካከላቸው አሁንም ርቀት መኖሩን ገልጿል። ኢራን በመጭዎቹ ቀናት ውስጥ ሀሳቧን እንደምታቀርብ የአሜሪካ ባለስልጣን ሲናገሩ አራግቺ ደግሞ ምላሹን በቀናት ውስጥ እንደሚያቀርቡ በትናንትናው ተናግረዋል።

ነገርግን የጦር ጄት ተሸካሚ መርከቦችን፣ ተዋጊ መርከቦችንና ጄቶችን የላኩት ትራምፕ ኢራን በኑክሌር መርሃግብር ጉዳይ ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ “መጥሮ ነገር” ይገጥማታል ብለዋል።  ትራምፕ ከ10-15 ቀን ቀነ ገደብ ያስቀመጡ ሲሆን ኢራን በበኩሏ የምትጠቃ ከሆነ በቀጣናው በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ስፈሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር እንደምትበቀል ዝታለች።

የአሜሪካና ኢራን ወደ ቀጥተኛው ጦርነት የሚገቡ ከሆነ በቀጣናው ከእስራኤል-ጋዛ ቀጥሎ ትልቁ አውዳሚ ይሆናል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው