Loading...

“ለእስራኤል አንዲት ሚሳኤል ትበቃታለች!” ኪም ጆንግ ኡን

በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሚመራው የፒዮንግያንግ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ እጅግ ጠንከር ያለና አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ኪም ጆንግ ኡን በሰጡት መግለጫ እስራኤል በአሜሪካ ድጋፍ በኢራን ላይ እየፈጸመችው ያለው ጥቃት “ሊታገሱት የማይቻል መስመር ያለፈ ነው” ሲሉ ኮንነዋል።

ሰሜን ኮሪያ ከኢራን ጋር ያላትን ወታደራዊ ወዳጅነት የምታጠናክርበትን ፍንጭ የሰጡት መሪው “ለእስራኤል ጥፋት አንዲት ሚሳኤል ብቻ ትበቃታለች” ሲሉ ዝተዋል።

ይህ የኪም ጆንግ ኡን መግለጫ የመጣው እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ “ታላቁ የውጊያ ዘመቻ” በጀመሩ ማግስት ነው።

ኢራን አሁን ላይ እየተጠቀመችባቸው ያሉት በርካታ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች የሰሜን ኮሪያ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መሆናቸው ይታወቃል።

ሰሜን ኮሪያ በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር አሜሪካ ትኩረቷን ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ እስያ እንድታዞር ጫና ልታደርግ ትችላለች።

ኪም ጆንግ ኡን እስራኤልን “በእሳት እንደምትጫወት ህጻን” በማለት የገለጿት ሲሆን ሀገራቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰድ እንደማትቆጠብ አስታውቀዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው