በእስራኤልና በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ምላሽ እየሰጠች ያለችው ኢራን ወደ ቱርክ ያስወነጨፈችው ባለስቲክ ሚሳይል በኔቶ የሚሳይልና የአየር መከላከያ ዩኒት መክሸፉን የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ሚሳይሉ ወደ ቱርክ አየር ክልል ያቀናው በኢራቅና በሶሪያ በኩል ነበር። በወደቀው የሚሳይል ስብርባሪ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የገለጸው ሚኒስቴሩ “መሬታችንንና የአየር ክልላችንን ለመከላከል” ያለማመንታት ሁሉም አስፈላጊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብሏል።
ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ መጠነሰፊ የአየር ድብደባ እያካሄደች ነው። በጥቃቱ እስካሁን የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሚኒ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል።
ኢራን ለዚህ አጸፋ የሰጠችው ወደ እስራኤል ድሮንና ሚሳይል በማስወንጨፍ እና በአረብ ባህረሰላጤ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችና ኢምባሲዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ነው።
ግጭቱ አሁንም ቀጥሏል።











