Loading...

ትራምፕ አሜሪካና ኢራን ግጭቱ በሚፈታበት  ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ እያካሄዱ ያለውን ግጭት በዘላቂነት መፍታት ባለፉት ሁለት ቀናት ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ጥልቅና ገንቢ የሆነው ውይይት ሳምንቱን ሙሉ እንደሚቀጥል ያስታወቁት ትራምፕ ዲፓርትመንት ኦፍ ዋር በኢራን የኃይል መሰረተልማት ላይ የሚያደርገውን ማንኛውንም ጥቃት ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንዲያቆም ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ ብለዋል።
ይህ የትራምፕ ትዕዛዝ በውይይቱ ውጤታማነት ላይ የተመሰረተ ነው።

እስራኤል ከአጋሯ አሜሪካ ጋር በኢራን ላይ መጠነሰፊ የአየር ጥቃት በመፈጸም የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን እንዲሁም ከአንድ ሺህ በላይ ንጹሃን መግደሏ ተዘግቧል።

ኢራን ይህን ጥቃት የተበቀለችው ወደ እስራኤልና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ወደሚገኙባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚሳይል ናዳ በማዝነብና መጠነሰፊ የድሮን ጥቃት በመፈጸም ነው። ኢራን በእስራኤል በፈጸመችው የድሮን ጥቃት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረትም ወድሟል። ኢራን በተለይ ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ዝግ ማድረጓን ካሳወቀችና በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረች በኋላ አለምአቀፉ የነዳጅ ዋጋ ንሯል። ይህ አሜሪካን ጨምሮ በመላው አለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል።

ትራምፕ ፍሬያማው ነው ያሉት ውይይት ጦርነቱን ያስቆመዋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው