Loading...

ትራምፕ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ያለመባረር ከለላ እንዲያቋርጡ ፍርድ ቤት ፈቀደላቸው

የአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለ500ዐ በላይ ኢትዮጵያውያንን ተሰጥቶ የነበረውን ከለላ (Temporary Protection Status-TPS), እንዲያቋርጡ በትናንትናው እለት ፈቅዶላቸዋል።

በቦስተን ግዛት የሚገኘው የአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት፣ ቀደም ሲል የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት(Homeland Security) የኢትዮጵያውያንን ጊዜያዊ ከለላ  ለማንሳት አሳልፎት የነበረውን አግዶት ነበር።

መስሪያቤቱ ጊዜያዊ ከለላዎችን ለማንሳት የወሰነዉ፣ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሰኔ ወር የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደር ጊዜያዊ ከላላዎችን እንዲያነሳ መፍቀዱን ነበር።ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ13 ሀገራት የመጡ ስደተኞች ጊዜያዊ ከለላ እንዲቋረጥ ለአሜሪካ ባለስልጣናት ይሁንታ ሰጥቶ ነበር።

የኢትዮጵያውያንን ጊዜያዊ ከለላ የማቋረጥ ውሳኔ በኢትዮጵያውያንና በአፍሪካ ማህበረሰብ የመብት ተሟጋች ቡድን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤቱ ጊዜያዊ ከለላውን ለማቋረጥ የወሰነው በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ ስለሆነ ኢትዮጵያውያን ይህን መብት ለማግኘት መስፈርቱን አያሟሉም በማለት ነበር።

“በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ አሁንም እንደቀጠለ ነው፤ ውሳኔው በአሜሪካ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት ከባድ አደጋ ላይ የሚጥል ነው”ሲሉ የቡድኑ ምክትል ዋና ዳሬክተር ዲያና ኮናቴ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በፌደራል ህግ መሰረት ጊዜያዊ ከለላ የሚሰጠው  የትውልድ ሀገራቸው በተፈጥሮ አደጋ፣ በትጥቅ ግጭት ወይም በሌሎች ከባድና ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ፣ ስደተኞች  ጊዜያዊ ከለላ ያገኛሉ። ይህን መስፈርት የሚያሟሉ ስደተኞች የሥራ ፈቃድ እንዲያገኙ እና  ከአሜሪካ መባረር ለጊዜው እንዲጠበቁ ያስችላል።

የቀድሞው የዴሞክራት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በ2022 በአሜሪካ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን የጊዜያዊ ጥበቃ ደረጃ ሰጥቷል። ይህም ውሳኔ የተወሰደው ኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭትና በከፍተኛ ሰብዓዊ ችግር ውስጥ በመሆኗ ዜጎቿን መጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ በመታየቱ ነበር።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው