Loading...

የቻይና አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት በ4.6 በመቶ አደገ

China’s GDP grows 4.6% in first nine months of 2026

የቻይና አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እ.ኤ.አ. በ2026 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት(ከጥር እስከ መስከረም) በ4.6 በመቶ አድጎ 107.1 ትሪሊዮን ዩዋን (16 ትሪሊዮን ዶላር) መድረሱን የቻይና ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮ (NBS) ሰኞ ያወጣው መረጃ አመለከተ።

በአጠቃላይ፣ ጫናዎች ቢኖሩም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የተረጋጋ የዕድገት አቅጣጫውን ማስቀጠሉን ቢሮው ገልጿል።

ከትላልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚገኘው ተጨማሪ እሴት ያላቸው ምርቶች በዓመት አንጻር የ5.3 በመቶ ዕድገት አሳይተዋል። ለአብነት፣ የመሣሪያዎች ማምረቻ ዘርፍ በ10.2 በመቶ፣ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ምርቶች አምራች ዘርፍ ደግሞ በ14.3 በመቶ አድጓል።

በተመሳሳይ ወቅት የ3ዲ ማተሚያ መሣሪያዎች፣ የሊቲየም-አዮን ባትሪዎችና የኢንዱስትሪ ሮቦቶች ምርት በቅደም ተከተል በ62.5 በመቶ፣ በ39.5 በመቶና በ29.1 በመቶ ጨምሯል።

የአገልግሎት ዘርፉም በዓመት አንጻር የ5.2 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። የኪራይና የንግድ አገልግሎቶች በ12.3 በመቶ፣ የመረጃ ማስተላለፍ፣ የሶፍትዌርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በ10.4 በመቶ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች በ5.8 በመቶ፣ እንዲሁም የመስተንግዶና የምግብ አቅርቦት አገልግሎቶች በ5.5 በመቶ አድገዋል።

የሀገሪቱን የፍጆታ እንቅስቃሴ ከሚያመለክቱ ዋና መለኪያዎች አንዱ የሆነው አጠቃላይ የሸቀጦችና አገልግሎቶች የችርቻሮ ሽያጭ በተመሳሳይ ወቅት በ2.6 በመቶ አድጓል። የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት፣ የገንዘብና የፋይናንስ አገልግሎቶች እንዲሁም የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ከ55 በመቶ በላይ ዕድገት አስመዝግበዋል። የጠቋሚ ንባቦቹ የሚያሳዩት የሀገሪቱ አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴ 50 ነጥብ(threshold) በላይ በሆነ የእድገት ውስጥ መሆኑን ነው።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቻይና የምታስገባቸውና ወደ ውጭ የምትልካቸው ዕቃዎች አጠቃላይ የንግድ መጠን በዓመት አንጻር በ18.8 በመቶ ጨምሮ 39.9 ትሪሊዮን ዩዋን ደርሷል።

ከዚህ አጠቃላይ የንግድ መጠን ውስጥ፣ በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ (BRI) ሥር ከሚገኙ አገራት ጋር የሚደረገው ንግድ በ17.1 በመቶ አድጓል።

ከጥር እስከ መስከረም ባለው ወቅት፣ በገጠር ከሚኖሩ ቤተሰቦች የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ሳይጨምር የቻይና ቋሚ ንብረት ኢንቨስትመንት በ7.2 በመቶ ቀንሷል። ሆኖም፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረቱ ዘርፎች ያለው ኢንቨስትመንት ጨምሯል።

በግለሰብ የፈጠራ ምርቶች ላይ ያለው ኢንቨስትመንት በ9.3 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ያለው ኢንቨስትመንት ደግሞ በ4.9 በመቶ ዕድገት አሳይቷል

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው