Loading...

ቻይና ብሪክስ ለአፍሪካ ሀገራት ያለውን ፋይዳ እንዴት እያጠናከረችው ነው?

China's role in BRICS for Ethiopia and Africa

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የመሠረቱት ብሪክስ፣ ከዚህ በፊት በአለም ደረጃ ገዥ ተደርገው ለሚወሰዱት ለምዕራባውያን ትርክቶችና አመለካከቶች የተለየ አማራጭ ሆኖ ብቅ ብሏል።

በታዳጊ ኢኮኖሚዎች የሚመራው ብሪክስ፣ ለደቡብ-ደቡብ ትብብር ቅድሚያ ይሰጣል። በብሪክስ ውስጥ አባል ሀገራት በዓለም አቀፍ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች በተለይም የጋራ ጥቅማቸውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ዕድል ያገኛሉ። በተጨማሪም ተደራድረው ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንደሚጠቅም የሚገልጹት በብዙ ወገኖች (Multilateral) ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ የዓለም ሥርዓት እንዲሰፍን ጥረት ያደርጋሉ። በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ባሩ ደምሴ፣ ብሪክስ የታዳጊ ኢኮኖሚዎችን ጥቅም የሚያሳድግና ፍትሐዊ የዓለም ሥርዓት እንዲፈጠር የሚገፋፋ መድረክ መሆኑን ይናገራሉ።

እንደ ኔቶ ካሉ በርካታ የምዕራባውያን ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥምረቶች በተለየ፣ ብሪክስ የታዳጊ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማሳደግ ቁርጠኛ ነው። በብዙ ሁኔታዎች፣ ከምዕራባውያን ተቋማት ጋር መሥራትና ከምዕራባውያን ሀገራት ጋር መደራደር ታዳጊ አገራት ከፍተኛ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲቀበሉ ሊጠይቅ ይችላል። ይህም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን ሊያዳክም ይችላል።

በተለይም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ጨምሮ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የምዕራባውያን ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መሣሪያዎች ሆነው እንደሚያገለግሉ ለረጅም ጊዜ ትችት ሲቀርብባቸው ቆይቷል። ይህ እነዚህ ተቋማት ለአፍሪካ ሀገራት ብድር ለመስጠት የገንዘብና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቻቸውን እንዲቀይሩ በሚያቀርቡት የቅድመ ሁኔታ ጥያቄዎች ታይቷል።

በደቡባዊ ንፍቀክበብ(Global South) በሚገኙ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራትና በምዕራባውያን ዓለም መካከል ያለው ግንኙነት ብዙውን ጊዜ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አጋርነትን አያንጸባርቅም ። በአንጻሩ በብሪክስ ውስጥ የሚሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት፣ ከአባል ሀገራት ጋር በሚያደርጉት ትብብር የሚገኙ ጥቅሞችን በፍትሐዊነት የማግኘት ዕድላቸው እንደሚሰፋ ያምናሉ።

ባሩ ደምሴ ብሪክስ ታዳጊ ኢኮኖሚዎች በእኩልነትና በመከባበር መርሆዎች ላይ ተመሥርተው የጋራ ጥቅምንና ልማትን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ተስማሚ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። ባሩ “ብሪክስ ታዳጊ ኢኮኖሚዎች የጋራ ጥቅምንና የጋራ ልማትን ለማሳደግ አስፈላጊ መድረክ ሆኗል” ብለዋል።

ሁሉን አቀፍ የሆነው ብሪክስ

በቅርብ ዓመታት ውስጥ የብሪክስ አባል ለመሆን ጥያቄ እያቀረቡ ያሉ ሀገራት ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። ይህ የሆነው ብሪክስ የበለጠ ሁሉን አቀፍ እየሆነ መምጣቱንና ለታዳጊ ሀገራት የልማት አጀንዳዎች የበለጠ ምላሽ በመስጠቱ ነው። “ታዳጊ ሀገራት በአጠቃላይ የበለጠ ወካይ፣ ሁሉን አቀፍና ለልማት ጉዳዮቻቸው የበለጠ ምላሽ የሚሰጥ ዓለም አቀፍ መድረክ ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል ባሩ።

ባሩ በንግድና በኢንቨስትመንት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በጤና፣ በዲጂታል ፈጠራ እና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ የብሪክስ ትብብር ውጤቶች በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ተጨባጭ ጥቅሞችን ሊያስገኙ እንደሚችሉ አንስተዋል። ባሩ አክለውም የብሪክስ ትብብር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ2030 ዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) እና የአፍሪካ ሕብረትን አጀንዳ 2063 ለማሳካት ወሳኝ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ገልጸዋል።

ባሩ እንዳሉት በአብዛኛው ወጣቶች የሚበዙባት አፍሪካ ከብሪክስ የትብብር ተነሳሽነቶች በከፍተኛ ሁኔታ ልትጠቀም ትችላለች። ስለዚህም የብሪክስ ሁሉን አቀፍ አካሄድ ኢኮኖሚያቸውን ለማጠናከርና የልማት አጀንዳዎቻቸውን ለመፈጸም ለሚሹ ታዳጊ ሀገራት ወሳኝ ነው።የብሪክስ ትብብርን በማጠናከር የቻይና ሚናየዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ ኢኮኖሚ የሆነችው ቻይና፣ በመሠረተ ልማት ልማት፣ በንግድና በቴክኖሎጂ ትብብር አማካኝነት ብሪክስ ለታዳጊ አገራት ያለውን ፋይዳ አጠናክራለች።

ቻይና በድህነት ቅነሳ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በመሠረተ ልማት ግንባታና በቴክኖሎጂ እድገት ያካበተችው ልምድ ለብዙ ታዳጊ አገራት ጠቃሚ ትምህርቶችን ሰጥቷል።

ባሩ “ ቻይና የእውቀት ልውውጥን፣ የአቅም ግንባታንና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት፣ የብሪክስ ትብብር ሥርዓት የልማት ትብብርንና የጋራ ብልጽግናን ለማሳደግ ስትራቴጂያዊ መድረክ እንዲሆን አግዛለች” ብለዋል።

ቻይና በተጨማሪም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች የብሪክስ ትብብርን ለማሳደግ ተነሳሽነቶችን ወስዳለች። ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በምታደርገው ትብብርም በእነዚህ ዘርፎች አይተኬ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።

ባሩ እንደገለጹት እነዚህ ተነሳሽነቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በቴክኒክ እውቀትና በቴክኖሎጂ አቅም ረገድ ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመቅረፍ ሊያግዟቸው ይችላሉ።እ.ኤ.አ. በ2024 የብሪክስ ሙሉ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ከቻይና ጋር ጠንካራና ሁሉን አቀፍ አጋርነት ገንብታለች። ይህ ግንኙነት የባቡር መስመሮችና አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ በዋና ዋና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ በሚደረግ ትብብር፣ እንዲሁም በንግድ ልውውጥ መስፋፋት ተጠናክሯል። ለዚህም ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ምርቶች ይፋ ያደረገችው የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ በከፊል አስተዋጽኦ አድርጓል።

መጭውን የብሪክስ ሊቀመንበርነት የምትረከበው ቻይና እ.ኤ.አ. በ2027፣ 19ኛውን የብሪክስ ጉባኤ ታስተናግዳለች። በዚህ ምክንያት ቻይና የቡድኑን የወደፊት አቅጣጫና የልማት ቅድሚያዎች በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ይኖራታል።

ቻይና የአፍሪካ አገራትን ኢኮኖሚያዊና የልማት ጥቅሞች ለማሳደግ ያለውን የብሪክስ ቁርጠኝነት አጠናክራለች። ከመሠረተ ልማት ግንባታና ከንግድ ጀምሮ እስከ ሰው ሠራሽ አስተውሎትና ዲጂታል አስተዳደር ድረስ ባሉ ዘርፎች ከአፍሪካ አገራት ጋር በሚያደርገው ትብብር፣ ቻይና ብሪክስ የደቡብ-ደቡብ ትብብር መድረክ ሆኖ እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አድርጋለች።

Share this article

Subscribe

By pressing the Subscribe button, you confirm that you have read our Privacy Policy.
Your Ad Here
Ad Size: 336x280 px

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው