Loading...

ኢትዮጵያና አሜሪካ የንግድና የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማስፋት ያለመ ውይይት አደረጉ

Ethiopia, US officials discuss expansion of trade, investment

ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ንግድን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር በአዲስ አበባ ተወያዩ።

ውይይቱ በገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋና በአሜሪካ ንግድ መምሪያ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት ጸሐፊ ማርክ ሚቸል በተመራ ልዑክ መካከል ተካሂዷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ውይይቱ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በአዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችና የአሜሪካ የግል ዘርፍ ተሳትፎን ስለማሳደግ ላይ ያተኮረ ነበር።

የኢትዮጵያ ወገን የንግድና የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለማሻሻል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን አብራርቷል። ሚቸል በበኩላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና የንግድ ግንኙነቱን ለማጠናከር የአገራቸው ፍላጎት መኖሩን ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ላይም ተወያይተዋል። የአሜሪካ የኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (EXIM) እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (DFC) ለፕሮጀክቱ ፋይናንስ ለማሰባሰብ እያደረጉ ያለውን ተሳትፎም አንስተዋል።

የሁለቱ አገራት ወገኖች የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ቀጣይ ውይይትና ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አረጋግጠዋል።

Share this article

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው